አሜሪካ ለእስራኤል የአውሮፕላን ነዳጅ በአየር ላይ የሚሞላ ታንከር ለመሸጥ ተስማማች
ይህ የአውሮፕላን ታንከር ከአሜሪካ እና ጃፓን ውጪ ያለው ሀገር የለም
እስራኤል ታንከሩ እጇ ሲገባ የአውሮፕላን ታንከር ያላት ሶስተኛዋ ሀገር ትሆናለች ተብሏል
አሜሪካ ለእስራኤል የአውሮፕላን ነዳጅ በአየር ላይ የሚሞላ ታንከር ለመሸጥ ተስማማች።
የአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ በበረራ ላይ ያለ አውሮፕላን ወደ ምድር ማረፍ ሳያስፈልገው ነዳጅ መሙላት የሚያስችል ዘመናዊ የአውሮፕላን ታንከር ለእስራኤል ለመሸጥ መስማማቷ ተገልጿል።
በዚህ ስምምነት መሰረት ቦይንድ አቪዬሽን ኩባንያ ለእስራኤል አየር ሀይል አራት የአውሮፕላን ነዳጅ ታንከር ትሸጣለች ተብሏል።
አሜሪካ ታንከሮቹን ለእስራኤል ለመሸጥ የወሰነችው ዋሸንግተን ከኢራን ጋር አዲስ ስምምነት ላይ እንደምትደርስ በመተማመን እንደሆነ ዘገባው አክሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ቤኒ ጋንትዝ ለአል ዐይን አረብኛው ክፍል እንዳሉት "ለዚህ ስምምነት አሜሪካንን ማመስገን እንፈልጋለን ፣ስምምነቱ ከኣራቱ የአውሮፕላን ነዳጅ ታንከሮች በተጨማሪ የጦር ሂልኮፕተር፣ የባህር ላይ ጦር መሳሪያ እና ሌሎች ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ከአሜሪካ እናገኛለን" ብለዋል።
ይህ አውሮፕላን በአየር ላይ እያለ ተጨማሪ ነዳጅ መሙላት የሚያስችሉት የአውሮፕላን ታንከሮች አሁን ላይ ከአሜሪካ እና ጃፓን በስተቀር ያለው ሀገር የለም ተብሏል።
በዚህ የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት እስራኤል ታንከሮቹን ከፈረንጆቹ 2025 እስከ 2026 ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እጇ ይገባልም ተብሏል።
እነዚህ የአውሮፕላን ታንከሮች 927 ሚሊዮን ዶላር ዋ እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን ወጪውን ራሷ አሜሪካ እንደምትከፍል አስታውቃለች።