ፖሊስ 65 ቶን ታንኩን በወታደራዊ ካምፕ አቅራቢያ በሚገኝ ቁሻሻ ውስጥ ተጥሎ አግኝቼዋለሁ ብሏል
የእስራኤል ጦር መርካቫ 2 የተባለ ግዙፍ ወታደራዊ ታንክ ተሰርቆት እንደነበረ አስታወቀ።
ማርካቫ 2 የተባለው ግዙፍ ወታደራዊ ታንክ በሰሜን እስራዔል ሃይፋ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ እንደጠፋም የእስራኤል ጦር አስታቋል።
የእስራኤል ፖሊስ እንዳለው 65 ቶን የሚመዝነውን ግዙፍ ወታደራዊ ታንክ በወታደራዊ ካምፕ አቅራቢያ በሚገኝ ቆሻሻ ስፍራ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል።
ከታንክ ስርቆት ጋር በተያያዘም ሁለት ሰዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል ሲል ኤ.ፒ ዘግቧል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ማርካቫ 2 ታንክ እንዴት ከወታደራዊ ማሰልጠኛ ቀጠና የተሰረቀ፤ አንዴትስ በበቆሻሻ ውስጥ ሊገኝ ቻለ የሚለውን ለማወቅ እየሞከሩ ነው።
የእስራኤል ጦር በጉዳዩ ላይ በሰጠው ማብራሪያ፤ ማርካቫ 2 የተባለው ግዙፍ ወታደራዊ ታንክ ከዓመታት በፊት ከአገልግሎት ውጪ እንደተደረገ እና መሳሪያ እንዳልታጠቀ አስታውቋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ታንኩ ለሰልጣኝ ወታደሮች እንደ መለማመጃ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱንም የእስራኤል ጦር ገልጿል።
ወታደራዊ የስልጠና ማዕከሉ ወታደረዊ ስልጠናዎች ሲኖሩ ለህዝብ ዝግ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ ነገር ግን ሰዎች በአካባቢው በቀላሉ ይተለላለፋሉ ተብሏል።