ፖለቲካ
ቱርክ፤ በሩሲያ እና ቻይና የሚመራው የጸጥታ ጥምረት አባል የመሆን አላማ እንዳላት ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተናገሩ
ኤስሲኦ በሩሲያ እና ቻይና የተመሰረተ የጸጥታ ጥምረት ነው
ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት በኡዝቤክስታን በተካሄደው የኤስሲኦ ስብሰባ ላይ ከተካፈሉ በኋላ ነው
የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የኔቶ አባል የሆነችውን ሀገራቸው የሻንጋይ ኮኦፐሬሽን ኦርጋናይዜሽን(ኤስሲኦ) አባልጰየማድረግ አላማ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ኤስሲኦ በሩሲያ እና ቻይና የተመሰረተ የጸጥታ ጥምረት ነው።
ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት በኡዝቤክስታን በተካሄደው የኤስሲኦ ስብሰባ ላይ ከተካፈሉ በኋላ መሆኑን ሮይተር ዘግቧል።
"በዚህ እርምጃ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ወደ ልዩ ቦታ ይደርሳል" ብሐዋል ፕሬዝደንት ኤርዶጋን።
ቱርክ በአሁኑ ወቅት ቻይና ሩሲያ ህንድ ፓኪስታን ኢራን ኪሪጊስታን ፓጃኪስታን ካዛኩስታን እና ኡዝቤኪስታን ያሉበት የጸጥታ ጥምረት የውይይት አጋር ነች።
በስብሰባው ላይ ከፕሬዝደንት ፒቲን ጋር የተነጋገሩት ኤርዶጋን በደቢብ ቱርክ በሚገኘው የኑክሌር ጣቢያ ጉዳይ የነበረውን ግጭት ለመፍታት ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸዋል።
በፈረንቹ 2001 የተቋቋመው በሩሲያ እና ቻይና የነበረ ሲሆን ከተመሰረተ ከአራት አመት በኋላ ህንድ እና ፓኪስታንን አካቷል፤ ይህም በቀጣናው ያለውን የምእራባውያን ጫና ለመቋቋም አላማ ያደረገ ነበር፡፡