እስራኤላዊያን መንግስታቸው ከሊባኖስ ጋር ያደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳበሳጫቸው ተናገሩ
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሂዝቦላህ ዳግም እንዲጠናከር እድል ሊሰጠው ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል ተብሏል
ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀው ጦርነት ለእስራኤል የበለጠ መጥቀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ገልጸዋል
እስራኤላዊያን መንግስታቸው ከሊባኖስ ጋር ያደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳበሳጫቸው ተናገሩ፡፡
የፍለስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር እስራኤል በይፋ ወደ ጦርነት የገባችው፡፡
የሊባኖሱ ሂዝቦላህ ከሐማስ ጎን መቆሙን ተከትሎ የተስፋፋው ይህ ጦርነት ከ13 ወራት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሷል፡፡
ይህን ስምምነት ተከትሎ ተፈናቅለው የነበሩ ሊባኖሳዊያን ወደ ቀድሞ ቤታቸው መጓዝ የጀመሩ ሲሆን ስምምነቱን የተቃወሙ እስራኤላዊያን ቁጥር ግን ቀላል አይደለም፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደጋፊዎች ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተቃውመዋል፡፡
ይሁንና በመላው እስራኤል በተደረገ ጥናት 37 በመቶ እስራኤላዊያን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሲደግፉ 31 በመቶዎቹ ተቃውመዋል ተብሏል፡፡
የኢራኑ ካሚኒ የእስራኤል መሪዎች የሞት ፍርድ እንዲጣልባቸው ጠየቁ
በተለይም ከሊባኖስህ ድንበር አቅራቢያ የተፈናቀሉ እስራኤላዊያን ወደ ቀድሞ መኖሪያ ቤታቸው ለመመለስ ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
እንደ ነዋሪዎቹ አስተያየት ከሆነ የሊባኖስ ጦር ወደ ቀድሞ ቦታዎቹ መግባቱ ሂዝቦላህ ዳግም እንዲጠናከር እና ጥቃት እንዲያደርስ እድል ሊሰጠው ይችላል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ጦርነቱ ሂዝቦላህ እንዲዳከም፣ ከሐማስ ጋር የነበረውን ጥልቅ ግንኙነት እንዲቋረጥ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በተለይም ሂዝቦላህ ለዓመታት ያከማቻቸው የጦር መሳሪያዎች እና መሰረተ ልማቶች በእስራኤል ጦር ጥቃት መውደማቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡