በአይፎን 16ም ሆነ በሌሎች የአይፎን ስልኮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የሚያደርገው ዋናው ምክንያት የማምረቻ ዋጋ መጨሩ ነው
የአፕል ስልክ ባለቤት መሆን ለምን እየከበደ መጣ?
የአይፎን 16 ስልክ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚኖረው የሚያሳዩ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ።
- ህንዳውያኑ ጥንዶች አይፎን ለመግዛት የ8 ወር ልጃቸውን ሽጠዋል
- አፕል በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳተላይት መልእት የሚልክ አይፎን 14 ይፋ አደረገ
የቀጣይ ትውልድ ስልክ የተባለው አይፎን 16 ዋጋው ባለማቋረጥ እንደሚጨምር የሚያሳዩ ሪፖርቶች መውጣታቸው አይፎን ስልክ መግዛት የማይቻልበት ጊዜ እየመጣ መሆኑን ያመለክታል።
እንደ ረፖርቶቹ ከሆነ አይፎን 15 ለማምረት የሚያስፈልገው ወጭ ሌሎች ስማርት ስልኮችን ለማምረት ከፈጀው ወጭ ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አሳይቷል።
ይህ የምርት ወጭ መጨመር የሚያመለክተው በሚቀጥለው አመት የሚመረቀው የአይፎን 16ም የማምረቻ ወጭም እንደሚጨምር ነው።
እንደ ኒኬ ዌብሳይት ከሆነ አይፎን16 ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ የማይቀር ነው። በአይፎን 16ም ሆነ በሌሎች የአይፎን ስልኮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የሚያደርገው ዋናው ምክንያት የማምረቻ ዋጋ መጨሩ ነው።
በቅርቡ ለገበያ የቀረበውን አይፎን 15 ፕሮ ማክስ ለማምረት የሚያስፈልገው ወጭ በዚህ አመት ወደ 588 ዶላር ከፍ ያለ ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ 2022 ለገበያ ከቀረበው አይፎን 14 የምርት ወጭ ጋር ሲነጻጸር የ12 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
የአይፎን ፕሮማክስ ሞዴሎችን ለማምረት የሚያስፈልገው ወጭ በፈረንጆቹ 2022 በ20 በመቶ ከመጨመሩ በፊት 2018-2021 ከ400 እስከ 500 ጭማሪ አሳይቷል።
የአይፎን ፕሮ ማክስ ካሜራ ዋጋ 30 ዶላር ሲሆን ይህም ከአይፎን 14 ካማራ ዋጋ በ380 በመቶ ጭማሪ አለው።