ስደተኞችን ወደ ሊቢያ የመለሰው ጣሊያናዊ የመርከብ ካፒቴን በእስር ተቀጣ
ካፒቴኑ 101 ስደተኞችን ከሜድትራኒያን ባህር ወደ ሊቢያ በመመለስ ለድንበር ጠባቂዎች አስረክቧል
ግለሰቡ ሰዎችን ለህይወታቸው አስጊ ወደ ሆነ ስፍራ መመለስን የሚከለክለውን ዓለም አቀፍ ህግ ጥሷል
ስደተኞችን ወደ ሊቢያ በመመለስ ለድንበር ጠባቂዎች ያስረከበው ጣሊያናዊው የመርከብ ካፒቴን የእስር ቅጣት እንደተላለፈበት ተነገረ።
ካፒቴኑ 101 ስደተኞችን በሜድትራኒያን ባር ላይ ከታደጋቸው በኋላ ለሊቢያ የድንብር ጠባቂዎች በማስረከቡ የ1 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል ነው የተባለው።
- የጣሊያን የባሕር ላይ ጠባቂዎች ከሊቢያ የተነሱ ከ500 በላይ ስደተኞችን ህይወት ታደጉ
- ከሊቢያ ድንበር የተነሱ 100 ስደተኞች በሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ
በእንደዚህ አይነት ወንጀል በጣሊያን ፍርድ ቤት ቀርቦ የቅጣት ውሳኔ ሲተላለፍ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ነው የተገለፀው።
ጁሴፔ ሶቲጉ የተባለው ግለሰቡ ሰዎችን ለህይወታቸው አስጊ ወደ ሆነ ስፍራ በግዳጅ መመለስን የሚከለክለውን ዓለም አቀፍ ህግ በመጣሱ ነው ጥፋተኛ የተባለው።
ጁሴፔ ‘ኤሶ 28’ የተባለች ነዳጅ አመላላሽ የጣሊያን መርከብ ካቴን ሲሆን፤ በወቅቱም ለሊቢያ ነዳጅ በማጓጓዝ ላይ ነበረ ተብሏል።
ካፒቴ በአውሮፓውያኑ ሀምሌ 2018 ላይ መነሻቸውን ከጣሊያን አድርገው ወደ ጣሊያን በመጓዝ ላይ የነበሩ 5 ነብሰ ጡሮች እና 5 ህጻናትን ጨምሮ 101 ስደተኞችን ጮኖ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሜድትራኒያን ባህር ላይ ከታደገ በኋላ ለሊቢያ ድንበር ጠባቂዎች አሳልፎ ሰጥቷል።
በፈረንጆቹ 2011 የሊቢያው መሪ ሙአማር ጋዳፊ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ በነገሰው አለመረጋጋትና ትርምስ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ በአብዛኛው አፍሪካዊ የሆኑ ስደተኞች ከሊቢያ ተነስተው ሜዲትራኒያንን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ይጓዛሉ።
በሊቢያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያዎች ባህር ከመስጠም በዳኑ ወይንም በሊቢያ የጸጥታ ኋይሎች በተያዙ ስደተኞች የተሞሉ ናቸው።
የፈረንጆቹ 2020 ብቻ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በሊቢያ ባህር ከመስጠም መትረፍ መቻላቸውን የተባሩት መንስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።