ኔይማርን ያሰናበተው አል ሂላል የሊቨርፑሉን አጥቂ ሞሀመድ ሳላህ ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ
የማችስተር ዩናይትዶቹ ካሴሚሮ እና ራስመስ ሆሉንድ በጣሊያን ክለቦች እየተፈለጉ ሲሆን ማርከስ ራሽፎርድ ከዩናይትድ ለመልቀቅ ክለብ እያፈላለገ ነው
በእለተ ረቡዕ የተሰሙ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች እና ጭምጭምታዎች ምን ይመስላሉ?
የጥር የዝውውር መስኮት ሊዘጋ ከአምስት ቀናት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የአምናው ሻምፒዮና ማንችስተር ሲቲ 125 ሚሊየን ፓውንድ ለ3 ተጫዋቾች ዝውውር በማውጣት በገቢያው ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከዚህ ባለፈ ቶትንሀም ፣ ብራይተን ፣ክሪስታል ፓላስ እና ዎልቭስ በዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙ ሌሎች ቡድኖች ናቸው፡፡
በእለተ ረቡዕ የተሰሙ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች እና ጭምጭምታዎች ምን ይመስላሉ?
- ሮማዎች የማንቸስተር ዩናይትዱን ብራዚላዊ አማካይ ካሴሚሮን እስከ የውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ በውሰት ማስፈረም ይፈልጋሉ፤ ነገርግን ዝውውሩ የተመሰረተው አርጀንቲናዊውን ኢንተርናሽናል ሊአንድሮ ፓሬድስን በመሸጥ ላይ ነው።
-ናፖሊ እና ጁቬንቱስ አዲሱን የማንችስተር ዩናይትድ አለቃ ሩበን አሞሪምን በበቂ አላስደሰተም የተባለውን ዴንማርካዊ የዩናይትድ የ21 አመት አጥቂ ራስሙስ ሆሉንድ ላይ አይናቸውን ጥለዋል፡፡
- ማንቸስተር ዩናይትድ የ20 አመቱን የሌሴ እና የዴንማርክ የክንፍ ተከላካይ ፓትሪክ ዶርጉን በ30 ሚሊየን ፓውንድ ለማስፈረም ተቃርቧል።
- የ27 አመቱ የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከኦልትራፎርድ ለመልቀቅ የብራይተኑን አጥቂ ዳኒ ዌልቤክን እንደ ወኪል በመቅጠር ክለብ እያፈላለገ ይገኛል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ራሽፎርድ በዚህ ወር ዩናይትድን ለመልቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ ወደ ጁቬንቱስ በውሰት መዛወር ነው።
- ከብራዚላዊው አጥቂ ኔማር ጁኒየር ጋር በስምምነት የተለያየው የሳኡዲው ክለብ አልሂላል የ32 አመቱን የሊቨርፑል ግብጻዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሞሃመድ ሳላህን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል፡፡
- ዎልቭስ የዝውውር ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ክለቦች ለብራዚላዊው አጥቂ ማቲዎስ ኩንሃ የሚያቀርቡትን ዋጋ እየጠበቀ ሲሆን፤ አስቶንቪላ፣አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎረስት የ25 አመቱን ተጫዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡
- የ19 አመቱ የባየር ሙኒክ አጥቂ ማቲስ ቴል ክለቡን በዚህ ወር መልቀቅ የሚፈልግ ሲሆን ቼልሲዎች ተጨዋቹን ለማስፈረም ከቡንደስሊጋው ቡድን ጋር እየተነጋገሩ ነው።
- ማንቸስተር ዩናይትዶች ራሽፎርድ ወይም አርጀንቲናዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች አሌሃንድሮ ጋርናቾ የሚሸጡ ከሆነ ማቲስ ቴልን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- የ22 አመቱ የማንቸስተር ሲቲ አማካኝ ጀምስ ማክቴ ከባየር ሙኒክ ተፈላጊነት ዝርዝር ውስጥ ወጥቷል፤ የቡንደስሊጋው ቡድን አርጀንቲናዊውን የ28 አመቱ ተጫዋች ኤሚሊያኖ ቡኤንዲያን ከአስቶን ቪላ ለማስፈረም ተዘጋጅቷል።
- ማንቸስተር ሲቲ የ24 አመቱን አንድሪያ ካምቢያሶን ለማስፈረም ፉክክር ገጥሞታል። ጁቬንቱስ በተጫዋቹ ዙሪያ የመጨረሻ ውሳኔውን የሚያሳውቀው ዛሬ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ከቤኒፊካ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በኋላ ነው፡፡
- ባየር ሙኒክ እና ማንቸስተር ዩናይትድ የ27 አመቱን የቼልሲ እና ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩን ለማስፈረም ይፈልጋሉ፤ የተጫዋቹ ዋጋ 70 ሚሊየን ፓውንድ ተገምቷል፡፡
- ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን የሊቨርፑል እና እንግሊዝ የቀኝ መስመር ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድን በጥር ወር ማስፈረም ባለመቻሉ ከዝውውር ገበያው ወጥቷል፡፡
በጥር የዝውውር መስኮት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች ዝውውር ወጪ ከባለፈው አመት ጋር ሲንጸጸር ከእጥፍ በላይ መጨመሩ ተሰምቷል፡፡
የፕሪምየር ሊግ ክለቦች በዚህ አመት ወጪ ያደረጉት 247 ሚሊየን ፓውንድ ከባለፈው አመት ከወጣው አጠቃላይ 90 ሚሊየን ፓውንድ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ የታየበት ነው፡፡
የዝውውር መስኮቱ ለአምስት ቀናት ክፍት ሆኖ መቆየቱን ተከትሎ ተጨማሪ የሚጠናቀቁ የተጫዋች ግዢዎች ወጪው ከዚህም ከፍ እንዲል ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
በጥር የዝውውር መስኮት ከፍተኛ የተጫዋቾች ዝውውር ወጪ ክብረወሰን የተያዘበት አመት 2023 ሲሆን በዚህ ጊዜ 815 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ ተደርጎ ነበር፡፡
የፉትቦል ትራንስፈር ዶት ኮም መረጃ እንደሚያመላክተው የአምናው ሻምፒዮና ማንችስተር ሲቲ 125 ሚሊየን ፓውንድ ለተጫዋቾች ዝውውውር በማውጣት በሊጉ በአጠቃላይ የወጣውን ወጪ ግማሽ ያህሉን ይሸፍናል፡፡