ፑቲን አውሮፓን አይፈራም ያሉት ዘለንስሲ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከዩክሬን ጎን እንዲቆሙ ተማጸኑ
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በባይደን አስተዳደር ስር የነበረችው አሜሪካ 60 ቢሊዮን የጸጥታ እርዳታ ጨምሮ የ475 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩክሬን ሰጥታለች
ከሳምንት በፊት ወደ ኋይትሀውስ የገቡት ፕሬዝደንት ትራምፕ እንዴት እንደሚያስቆሙት ባያብራሩም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን እንደሚያስቆሙ ቃል መግባታቸው ይታወሳል
ፑቲን አውሮፓን አይፈራም ያሉት ዘለንስሲ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከዩክሬን ጎን እንዲቆሙ ተማጸኑ።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ዩክሬን አስተማማኝ የጸጥታ ዋስትና እንደምትፈልግና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን አውሮፓን እንደማይፈሩ መናገራቸውን ሮይተርስ ፎክስ ኒውስን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዘለንስኪ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ከዩክሬን ጎን እንዲቆሙ መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ከሳምንት በፊት ወደ ኋይትሀውስ የገቡት ፕሬዝደንት ትራምፕ እንዴት እንደሚያስቆሙት ባያብራሩም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን እንደሚያስቆሙ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ትራምፕ የሩሲያውን መሪ ማግኘት ከማይሹት የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በተቃራኒ ፑቲንን አግኝተው ጦርነቱ ስለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር ፍቃደኝነታቸውን ገልጸዋል።
የትራምፕ ምርጫ ማሸነፍ ሞስኮ ከየካቲት 2022 ጀምሮ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" እንደሚያስቆም ተስፋ ቢያጭርም፣ ፈጥኖ ወደ ስምምነት መምጣት ዩክሬንን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላታል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
"ትራምፕ ከፍትህና ከዩክሬን ጎን እንዲቆም እንፈልጋለን" ሲሉ ዘለንስኪ ትናንት ማታ በተላለፈው የፎክስ ኒውስ ቃለ ምልልሳቸው ተናግረዋል። "ፑቲን አውሮፓን አይፈራም" ብለዋል ዘለንስኪ።
ዘለንስኪ ዩክሬን ለሩሲያ ወራራ እውቅና እንደማትሰጥ፣ ነገርግን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደምትመርጥ ተናግረዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በባይደን አስተዳደር ስር የነበረችው አሜሪካ 60 ቢሊዮን የጸጥታ እርዳታ ጨምሮ የ475 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩክሬን ሰጥታለች። እርዳታው በትራምፕ አስተዳደር ስር በተመሳሳይ መጠን መቀጠሉ አጠራጣሪ ሆኗል።