የአሜሪካ ወታደሮች ከ77 ዓመት በፊት ከጣልያን የወሰዱትን ኬክ መለሱ
በአሜሪካ ወታደሮች የተወሰደው ይህ ኬክ ለአንዲት የ13 ዓመት ታዳጊ ልደት የተዘጋጀ ነበር ተብሏል
ወታደሮቹ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከጣልያኗ ሳን ፔትሮ መንደር ነበር የልደት ኬኩን የወሰዱት
የአሜሪካ ወታደሮች ከ77 ዓመት በፊት ከጣልያን የወሰዱትን ኬክ መለሱ፡፡
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተካሄደበት በፈረንጆቹ 1945 ወቅት የአሜሪካ ወታደሮች ጣልያን ከሚገኙት ከጀርመን ወታደሮች ጋር ውጊያ ለማድረግ ያቀናሉ፡፡
ጦርነቱ ከመካሄዱ በፊት ግን በሰሜናዊ ጣልያን ግዛት ስር ባለችው የሳን ፔትሮ መንደር ነዋሪ የሆነች የአንዲት የ13 ዓመት ታዳጊ ልደት መከበር ይጀመራል፡፡ ታዳጊዋ ሜሪ ሚዮን ትሰኛለች፡፡
የሜሪን ልደት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ሳለ በድንገት ውጊያ ይጀመራል፡፡ ውጊያው በወቅቱ ዓለም በሁለት ጎራ ሆና እያካሄደችው ባለው የዓለም ጦርነት አካል በነበሩት በአሜሪካ እና በጀርመን ወታደሮች መካከል ነበር የተጀመረው፡፡
በዚህን ጊዜ ነበር የአሜሪካ ወታደሮች ለ13 ዓመቷ ታዳጊ ተዘጋጅቶ የነበረውን የልደት ኬክ የወሰዱት፡፡ይህ ክስተት ከተፈጠረ ከ77 ዓመት በኋላም የአሜሪካ ጦር በወቅቱ የ13 ዓመት ለነበረችው አሁን ላይ 90 ዓመት ለሞላት ሜሪ ሚዮን ለተወሰደባት ኬክ ምትክ የሚሆን አዲስ ኬክ ሰጥቷታል፡፡
በ6 ሺህ ዶላር የተሸጠው የዓለማችን ውዱ “ሐብሐብ”
የአሜሪካ ወታደሮች የኬክ ስጦታውን በአካል ወደ ጣልያን ቪሴንዛ ፓርክ በማምጣት የሜሪ ሚዮን 90ኛ ዓመት ልደት በዓልን አብረው አክብረዋል፡፡
በዚህ ታሪካዊ ክስተት ላይ ሜሪ ሚዮንን ጨምሮ የአሜሪካ ጦር አባላት፣የጣልያን መንግስት ባለስልጣናት፣ ጡረተኛ ወታደሮች እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል ሲል ሲኤኤን ዘግቧል፡፡
ቁመታቸው በአማካኝ 2 ሜትር በላይ የሆነው “የዓለማችን ረጅሙ ቤተሰብ”
ከ77 ዓመት በፊት የአሜሪካ እና የጀርመን ወታደሮች በሳን ፔትሮ መንደር ባካሄዱት ውጊያ 17 ወታደሮች እንደተገደሉ ዘገባው አክሏል፡፡
የ90 ዓመቷ ሜሪ ሚዮን በበኩሏ ይሄንን ታሪካዊ እና አይረሴ ኬክ ከቤተሰቦቼ ጋር ሆነን እናጣጥመዋለን ስትል መናገሯንም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡