ከእናታቸው ቤት አልወጣም ያሉ ጎልማሳ ልጆች በፍርድ ቤት ውሳኔ ተባረሩ
ልጆቹ ስራ እና ጥሩ ገቢ ቢኖራቸውም ከእናታቸው ቤት የመውጣት ፍላጎት እንዳልነበራቸው ተገልጿል
ብቻዬን ልኑርበት ያለችው እናትም በመጨረሻም ነጻነቴን አግኝቻለሁ ብለዋል
ከእናታቸው ቤት አልወጣም ያሉ ጎልማሳ ልጆች በፍርድ ቤት ውሳኔ ተባረሩ፡፡
የ75 ዓመት አዛውንቷ ጣልያናዊት ሁለት ወንድ ልጆች ያላቸው ሲሆን ህይወታቸውን ከነዚህ ልጆቿ ጋር ስትመራ ቆይታለች፡፡
በጥሩ ስነምግባር አሳድጌያቸዋለሁ እንዲማሩ እና በራሳቸው እንዲተማመኑ አድርጌ አሳድጉያቸዋለሁም ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የ40 እና የ42 ዓመት እድሜ ያላቸው እነዚህ ሁለት ልጆች ጥሩ ስራ እና ገቢ ቢኖራቸውም የቤቱን አስቤዛ የሚሸፍኑት ግን እኝህ አዛውንት ናቸው፡፡
እነዚህ ጎልማሶች ለአስቤዛ እንዲያዋጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ማለታቸው አዛውንቷን ቤቴን ልቀቁ እና የራሳችሁን ህይወት ምሩ ለማለት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ይሁንና እነዚህ ጎልማሶች እናታቸውን ከመርዳት ይልቅ ከጡረታ የምትገኝን ትንሽዬ ገንዘብ መጋራትን መምረጣቸው ተገልጿል፡፡
ብሪታንያ፣ ጃፓንና ጣልያን የጋራ ተዋጊ ጄት ለማምረት ተስማሙ
በጎልማሳ ልጃቸው የተማረሩት እኝህ እናትም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘውት እንደሄዱ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጎልማሳ ልጆቼ ከቤት ይባረሩልኝ በሚል ከወላጅ እናታቸው የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ጎልማሶቹ ከቤት እንዲባረሩ መወሰኑ ተገልጿል፡፡
በጣልያን ከወላጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ጎልማሶች ቁጥር ከፍተኛ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እድሜያቸው ከ18-34 ዓመት ከሆናቸው ልጆች ውስጥ 70 በመቶዎቹ አሁንም ከወላጆቻቸው ጋር ይኖራሉ፡፡
ባምቦሲዮኒ በጣልያንኛ በፖለቲከኞች ዘንድ የተለመደ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ትልቅ ህጻን ማለት ነው፡፡
ፖለቲከኞች ከወላጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ልጆችን በመተቸት የሚታወቁ ሲሆን መንግስት ትዳር ለሚመሰርቱ እና ልጆችን ለሚወልዱ ወጣቶች ማበረታቻዎችን መስጠጥ የሚያስችል ህግም አጽድቋል፡፡