የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ በሰራቸው ተዓምራት ቅዱስ ተብሎ ተሰየመ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርሎ አኩቲሰን ታማሚዎችን ፈውሷል በሚል ከቅዱሳን አንዱ እንዲሆን ወስናለች
የጌታ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚል ስያሜ የነበረው አኩቲሰን ከ18 ዓመት በፊት ነበር በሳምባ ምች ህይወቱ ያለፈው
የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ በሰራቸው ተዓምራት ቅዱስ ተብሎ ተሰየመ፡፡
በለንደን የተወለደው ካርሎ አኩቲስ ገና በ15 ዓመቱ ነበር በሳምባ ምች ህይወቱ ያለፈው፡፡
የትኛውንም ዕምነት ከማይሚከተሉ ቤተሰቦቹ የተወለደው አኩቲስ ገና በልጅነቱ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያም ነበር፡፡
ይህ ታዳጊ የኮምፒውተር ሙያውን በመጠቀም የካቶሊክ ዕምነትን በማስፋፋት ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል የተባለ ሲሆን የፈጣሪን ህያዊነት አረጋግጫለሁ በሚል ስብከቱም ይታወቃል፡፡
ታዳጊው ህይወቱ ካለፈ በኋላ የተቀበረበት አፈር ታማሚዎችን ፈውሷል መባሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳን መካከል አንዱ እንዲሆን እንድትወስን አድርጓታል፡፡
የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት የሮማ ሊቀ ጳጳስ ተመሳሳይ ፆታ ጥንዶችን በተመለከተ ያወጡትን አዋጅ ውድቅ አድረጉ
ሲኤን ኤን እንደዘገበው ከሆነ በጣልያኗ አሲሲ ከተማ የሚገኘው የዚህ ታዳጊ መቃብር አፈር አንድ ኮስታሪካዊት ሴት ካለባት የዐዕምሮ ህመም እንድትፈወስ ረድቷል፡፡
እንዲሁም ሲወለድ ጀምሮ ባለበት የጣፊያ ህመም ምክንያት ምግብ መመገብ ያልቻለ አንድ ብራዚሊያዊ መፈወሱን ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ የታዳጊው መቃብር አፈር በሁለት ሰዎች ላይ የሰራውን ተዓምር ካረጋገጠች በኋላ በፖፕ ፍራንሲስ ሰብሳቢነት ከቅዱሳን መካከል አንዱ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
በቀጣይም ቅዱስ አኩቲስ የሚከበርበት እና የሚታሰብበት ዕለት እና ቀን ለዕምነቱ ተከታዮች ፋ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ውሳኔ ከወጣት ካቶሎካዊያንን ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ሊያነቃቃ እንደሚችል በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡
ቅዱስ እንዲሆን የተወሰነው አኩቲስ በልጅነት እድሜው የኮምፒውተር ጌሞችን መጫወት ያዘወትር እንደነበር አብረውት ያሳለፉት ጓደኞቹ ተናግረዋል፡፡