ጣሊያን ከ53 ዓመታት ቆይታ በኋላ 2ኛ የአወሮፓ ዋንጫዋን ማንሳት ችላለች
ጣሊያን የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ በፈረንጆቹ በ1968 ነው ማንሳት የቻለችው
ጣሊያን እንግሊዝን በመርታ የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒየን ሆናለች
ጣሊያን ሁለተኛውን የአውሮፓ ዋንጫዋን ከ53 ዓመታ ቆይታ በኋላ በትናንትናው እለት ማንሳት ችላለች።
ይህም በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ አንድ ሀገር ዋንጫ ለማሳት የጠበቀችው ረጅሙ ዓመት እንደሆነም ነው የተነገረው።
የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በትናንትው እለት ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን፤ የፍጻሜ ጨዋታውም ጣሊያንን ከእንግሊዝ አገናኝቶ ነበር።
በጨዋታውም ጣሊያን እንግሊዝን በመለያ ምት በመርታት የአውሮፓ ዋንጫን ከ53 ዓመታ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ማንሳት ችላለች።
በጨዋታውም መደበኛው 90 ደቂቃ እና ጭማሪ 30 ደቂቃ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠ መለያ ምት ጣሊያን 3 ለ 2 አሸንፋ ነው የአውሮፓ ሻምፒዮና መሆኗን ያረጋጠቸው፡፡
ይህ የ2006ቱ የዓለም ዋንጫ ባለቤት በሆኑት ጣሊያኖች የአውሮፓ ዋንጫን ከ1968 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳካት ችለዋል።
ጣሊያን የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ በፈረንጆቹ በ1968 ማንሳት የቻለች ሲሆን፤ በጨዋታውም ዩጎዝሎቫኪያን በመርታ ነው የዋንጫው ባለቤት መሆን የቻለችው።
ከዚህ ውጪ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫ ሁለት ጊዜ ለፍጻሜ ጨዋታ ደርሶ ዋንጫውን ሳያነሳ ቀርቷል።
ይህም በአውሮፓውያኑ በ2000 ከፈረንሳይ ጋር ለፍጻሜ ደርሰው የተሸነፉ ሲሆን፤ በ2012 ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር ለፍጻሜ ደርሰው ነበር።