እንግሊዝ ከ55 ዓመታት በኋላ በአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ ደረሰች
እንግሊዝ ዴንማርክን 2ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ነው ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ መድረስ የቻለችው
የእንግሊዝ ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም አቀፍ መድረክ ለፍጻሜ ጨዋታ የደረሰቸው በአውሮፓውያኑ በ1966 ነበር
እንግሊዝ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ከ55 ዓመታት ቆይታ በኋላ ትናነት ምሽት በተደረገ ጨዋታ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ደርሳለች።
እንግሊዝ ትናት ምሽት በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዴንማርክን በመርታት ነው ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ለመድረስ የበቃችው።
ትናንት ምሽት በዊንብሌይ በተካሄደው ጨዋታ ዴንማርክ ዳምስጋርድ በ30ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል መምራት ችላ ነበር።
ሆኖም ግን የዴንማርኩ ተጫዋች ካየር በ39ኛው ደቂቃ ላይ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ እንግሊዝን ከዴንማርክ ጋር አቻ አደረጋት።
መደበኛው 90 ደቂቃም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሀሪኬን በተጨማሪ ሰዓት ላይ ለእንግሊዝ የተሰጠን ፍጹም ቅጣት ከመረብ በማሳረፍ እንግሊዝን አሸናፊ ማድረግ ችሏል።
ጨዋታውንም እንግሊዝ ዴንማርክን 2ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ለአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ መድረስ ችላልች።
በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታም የፊታችን እሁድ ምሽት በዌምብሌይ ስታዲየም እንግሊዝ ከጣሊያን የሚፋለሙ ይሆናል።
የእንግሊዝ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ለፍጻሜ ለመድረስ 55 ዓመታትን መጠበቅ የግድ ሆኖበት ቆይቷል።
የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም አቀፍ መድረክ ለፍጻሜ ጨዋታ ደርሶ የነበረው በአውሮፓውያኑ በ1966 የዓለም ዋንጫ ሲሆን፤ በወቅቱም ከምእራብ ጀርመን ጋር ነበር የተጫወተው።