ፖለቲካ
የጣሊያኗ ሚላን የሳይክል አደጋን ለመቀነስ በአውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ 'መለያ' አስተዋወቀች
ከባድ ተሽከርካሪዎች መለያና ማስጠንቀቂያ ካለጠፉ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል
ህጉ በዋና ዋና ክፍሎች ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት እንደሚተገበር ተነግሯል
ሚላን ከተማ በሳይክል ተጠቃሚዎች ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመቀነስ ለአሽከርካሪዎች በማይታዩ ቦታዎች ላይ 'መለያ ሴንሰር' እንዲተከሉ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።
ከተማዋ አውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎች መለያውን እንዲገጥሙ አስገድዳለች።
ሰኞ ተፈጻሚነቱ ይጀምራል የተባለው አዲሱ ህግ አውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎች መለያና ማስጠንቀቂያ ካለጠፉ እንዲንቀሳቀሱ አይፈቅድም ተብሏል።
በተለይም በዋና ዋና የከተማዋ አካባቢዎች ከሰኞ እስከ አርብ እና በስራ ሰዓቶች አስገዳጁን መመሪያ የማያከብሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለዋል።
ሳይከል በሚያሽከረክሩና በእግረኞች ላይ የሚደርሰው አደጋ በመበራከቱ በከተማዋ ተቃውሞ አስነስቷል።
አሽከርካሪዎች ከአዲሱ ህግ ጋር እስኪላመዱ ድረስ የተወሰነ ጊዜ ይሰጣታቸዋል ተብሏል።
ሜትሮፓሊታንቷ የጣሊያን ከተማ ሚላን የአየር ብክለትንና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ በአንዳንድ የከተማዋ ቦታዎች ለማሽከርከር የሚከፈለው ክፍያ ላይ ማሻሻያ አድርጋለች።
ሚላን ከፍተኛ የአየር ብክለት ያለባት ከተማ ስትሆን፤ የአውሮፓ ህብረት ካስቀመጠው ደረጃ በታች የሆነ አየር አላት።