ጣሊያን በቀብር ስነ-ስርአት ላይ ጥላው የነበረውን እግድ ማንሳቷን አስታውቃለች
ጣሊያን በቀብር ስነ-ስርአት ላይ ጥላው የነበረውን እግድ ማንሳቷን አስታውቃለች
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በርካታ ዜጎቿን ያጣቸው ጣሊያን የቀብር ሥነ-ስርዓትን ልትፈቅድ መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በሰጡት መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ተጥሎ የነበረው የቀብር ሥነ ስርዓት ገደብ ይነሳል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት 15 የቤተሰብ አባላት ባሉበት ሥርዓተ ቀብር ይፈጸማል ተብሏል፡፡
ይህም በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከግንቦት 4 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት የሚካሄደው በሳይንቲፊክ ኮሚቴ ታይቶ ነው ብለዋል፡፡
የቤተ እምነት መሪዎች ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴን ወሳኔ መቃወሟቸው ተሰምቷል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ግን ሁኔታዎች እየታዩ ማስተካከያዎች እንደሚደረጉ ማስታወቁን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች የቀብር ሥነ ስርዓት የሚካሄደው በመንግስት የነበረ ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ላለማስፋፋት በሚል ቤተ-ዘመድ መሳተፍ አይችልም ነበር፡፡
እስካሁን በጣሊያን ከ26ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል፡፡