ከኮሮና ያገገሙ ስዎች ድጋሚ እንደማይያዙ የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም- የአለም ጤና ድርጅት
ድርጅቱ መንግስታት የአደጋ ስጋት ነፃ የሚል ሰርተፊኬት ላገገሙ ሰዎች መስጠት እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል
የአለም ጤና ድርጅት ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ድጋሚ ከመያዝ የሚከላከልላቸው መድህን ስለማዳበራቸው የሚያሳይ መረጃ የለም ብሏል
የአለም ጤና ድርጅት ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ድጋሚ ከመያዝ የሚከላከልላቸው መድህን ስለማዳበራቸው የሚያሳይ መረጃ የለም ብሏል
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከበሽታው ካገገሙ በኋላ በድጋሚ በቫይረሱ ከመያዝ የሚያድናቸው የበሽታ መከላከያ መድህን ማዳበራቸውን የሚያሳይ ምንም መረጃ አለመኖሩን የአለም ጤና ድርጅት በዛሬው እለት አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በሰጠው ሳይንሳዊ መግለጫ መንግስታት የአደጋ ስጋት ነፃ የሚል ሰርተፊኬት ላገገሙ ሰዎች መስጠት እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል፤ ምክንያቱም ትክክለኛነቱ ስለማያስተማምን ነው ብለዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት እንዳለው ከሆነ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ችላ ስለሚሉት ቫይረሱ የበለጠ እንዲስፋፋ እድል ይሰጣል ብሏል፡፡
ድርጅቱ አንዳንድ መንግስታት ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች በድጋሚ ከመያዝ ነፃ ናቸው የሚለው ሰርተፊኬት በመስጠት ሰዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ወይንም እንዲጓጓዙ አስበው መሆኑን ገልጿል፡፡
ችሊ ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀችው ከኮሮና ቫይረስ ላገገሙ ሰዎች የጤና ስርተፊኬት እንደምትሰጥ ገልፃ ነበር፡፡ያገገሙት ሰዎች የመከላከያ አቅም መገንባታቸው ሲረጋጠጥ ወደ ስራ መመለስ ይችላሉ፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በቫይረሱ ተይዞ ያገገመ ሰው ድጋሚ እንዳይያዝ የሚያስችለውን መድህን ስለመገንባቱ ወይንም ስለመገንባቱ መረጃዎቹን እንደሚያያቸው አስታውቋል፡፡ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ 2.8 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፣ 196,298 ሰዎቸ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ድርጅቱ አብዛኞቹ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች መድህን ይኖራቸዋል፡፡ ነገርግን አንዳንዶቹ ዝቅተኛ አቅም ያለው መድህን አላቸው ብሏል ድርጅቱ፡፡