ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት የአሜሪካ ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይተኩ አስጠነቀቁ
ትራምፕ ሀገራቱ የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው ዶላርን መጠቀም የሚያቆሙ ከሆነ መቶ በመቶ ቀረጥ ይጣልባቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል

ትራምፕ ዶላርን ላለመጠቀም የወሰኑ ሀገራት ከአሜሪካ ገበያ እንደሚሰናበት መጠበቅ አለባቸው ብለዋል
ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት የአሜሪካ ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይተኩ አስጠነቀቁ።
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክ አባል ሀገራት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይጠቀሙ ወይም የአሜሪካ ዶላርን የሚተካ ሌላ ገንዘብ እንዳይጠቀሙ እንደሚፈልጉ በትናንትናው ተናግረዋል።
ትራምፕ ሀገራቱ የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው ዶላርን መጠቀም የሚያቆሙ ከሆነ መቶ በመቶ ቀረጥ ይጣልባቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
"እነዚህ ሀገራት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ እንደማያስተዋውቁ፣ የአሜሪካ ዶላርን የሚተካ ሌላ ገንዘብ እንደማይደግፉ እንዲያረጋግጡልን እንፈልጋለን" ያሉት ትራምፕ ይህ የማይሆን ከሆነ ወደ አሜሪካ በሚያስገቡት እቃ ላይ መቶ በመቶ ቀረጥ እንደሚጣልባቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ ዶላርን ላለመጠቀም የወሰኑ ሀገራት ከአሜሪካ ገበያ እንደሚሰናበት መጠበቅ አለባቸው ብለዋል።
"ልላ አማራጭ ካለ መጠቀም ይችላሉ። ብሪክስ ዶላርን በአለምአቀፍ ገበያ የሚተካበት መንገድ የለም፤ የሚሞክር ሀገር ካለ ከአሜሪካ መሰናበት አለበት" ብለዋል ትራምፕ።
በምዕራባዊውያን የበላይነት የተያዘውን የአለም ስርአት ለመገዳደር የተቋቋመው እና የእስያዎቹን ኃያላን ቻይና እና ሩሲያን ያካተተው ብሪክስ ዶላርን ከገበያ ለማስወጣት ወይም ጎንለጎን አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ለማስተዋወቅ እየሰራ ነው።