የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልጅ የግል ረዳት በቫይረሱ ተይዘዋል
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ልጅ የግል ረዳት በኮሮና ተይዘዋል
ኮሮና ቫይረስ ኋይት ሃውስን ማንኳኳቱን ቀጥሏል፡፡ በባለስልጣናቱ አቅራቢያ ያሉ የ“ነጩ ቤተ መንግስት” አንዳንድ የአመራር አካላትም በቫይረሱ መያዛቸው እየተነገረ ነው፡፡
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ የግል ረዳት በቫይረሱ መያዛቸውን ሲ.ኤን.ኤን የቤተ መንግስቱን ምንጮች ዋቢ አድርጎ ትናንት ዘግቧል፡፡
ግለሰቡ የቫይረሱን ምልክቶች በውል የማያሳዩ (asymptomatic) ቢሆንም በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ በመረጋገጡ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡
ኢቫንካና ባለቤታቸው ያሬድ ኩሽነር ግን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ስለመረጋገጡ ተነግሯል፡፡
ኢቫንካ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ፎቶ፡ ኢቫንካ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት
(ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ኢቫንካ እና አምባሳደር ማይክ ራይነር)
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የምክትላቸው የማይክ ፔንስ የፕሬስ ጉዳዮች ኃላፊ (press secretary) ካቲ ሚለር በቫይረሱ ስለመያዛቸው ትናንት አስታውቀዋል፡፡
ካቲ በኋይት ሃውስ የፕሬዝዳንቱ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች አማካሪ የስቴፈን ሚለር ባለቤት ናቸው፡፡
ቫይረሱ በአንዳንድ የፕሬዝዳንቱ አጃቢዎች ዘንዳ ስለመገኘቱም ሰሞኑን ሲወራ የነበረ ነገር ነው፡፡
በአሜሪካ 1 ነጥብ 2 ሚሊዬን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 77 ሺ 200 ሰዎች ሞተዋል፡፡