የ8 ዓመቱ ታዳጊ ቀዳሚው የዩቲዩብ ከፍተኛ ተከፋይ ሆነ
የህጻናት መጫዎቻዎችን በተመለከተ ትንታኔን የሚሰጠው ርያን ካጂ ሊጠናቀቅ በተቃረበው የፈረንጆቹ 2019 ከታክስ በፊት 26 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማግኘት ቀዳሚው ዩቲዩበር ስለመሆኑ ፎርብስ አስነብቧል፡፡
ገቢው ባለፈው ዓመት ካገኘው 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብልጫ ያለው ነው፡፡
“የርያን ዓለም” (Ryan’s World) በሚል በስሙ የተከፈተው የሪያን የዩቲዩብ ቻናል 22 ነጥብ 9 ተመዝጋቢዎች (Subscribers) አሉት፡፡
ጎግል በተሰኘው የመፈለጊያ ድረ ገጽ ባለቤትነት በሚተዳደረው ዩቲዩብ የዓመቱ ቀዳሚ ከፍተኛ ተከፋይ የተባሉ 10 ዩቲዩበሮች በድምሩ 162 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘታቸውንም ፎርብስ ይፋ አድርጓል፡፡
ከአሁን ቀደም በቀዳሚ ዩቲዩበርነቱ እና በከፍተኛ ገቢው ይታወቅ የነበረው ‘ፔው ዳይ ፒ’ (Pew Die Pie) ከሌላኛው ዩቲዩበር ፌሊክስ ጄልበርግ ጋር በጥምረት በ13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ከፍተኛ ተከፋይ የተባሉ ቀዳሚዎቹ አስር ዩቲዩበሮች ( YouTube's biggest earners of 2019)
ተከታዮቹ ናቸው፡-
1 -- ርያን ካጂ, $26 ሚሊዮን
2 -- ዱድ ፐርፌክት, $20 ሚሊዮን
3 -- አናስታሺያ ራድዝኒስካያ, $18 ሚሊዮን
4 -- ርሄት እና ሊንክ, $17.5 ሚሊዮን
5 -- ጄፍሪ ስታር, $17 ሚሊዮን
6 – ፕሬስተን (Preston Arsement), $14 ሚሊዮን
7 (በጥምረት) -- ‘ፔው ዳይ ፒ’ (Pew Die Pie) (ፌሊክስ ጄልበርግ), $13 ሚሊዮን
7 (በጥምረት) -- ማርኪፕሊየር (Mark Fischbach), $13 ሚሊዮን
9 -- ዳን ቲዲኤም (DanTDM-Daniel Middleton), $12 ሚሊዮን
10 -- ቫኖስ ጋሚንግ (Evan Fong), $11.5 ሚሊዮን
ምንጭ፡- ሲኤንኤን