የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክስ ሂደት ምን ይመስላል?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን እንዲነሱ በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰሱ (ኢምፒችመንት የተካሄደባቸው) በታሪክ ሶስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡
ኮንግረሱ ትናንት በፕሬዝዳንቱ ሁለት ክሶች ላይ ትናንት ታህሳስ 08 ቀን 2012 ዓ.ም. ለ12 ሰዓታት ያክል የዘለቀ ክርክር ካደረገ በኋላ ነው በፕሬዝዳንቱ ቀጣይ እጣ ፋንታ ዙሪያ ድምጽ የሰጠው፡፡
ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን ለላይኛውምክር ቤት ለሴኔቱ መርቷል፡፡ በኮንግረሱ የውሳኔ ሂደት ወቅት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ክሳቸውን የአክራሪ ግራ ዘመሞች የወረደ ውሸት እና በሪፓብሊካን ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሲሉ በተደጋጋሚ በተዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡