የተሰናበቱት ሹማምንት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትርና መንግስት እስኪሾም ድረስ በጊዜያዊነት ይቆያሉ ተብሏል
የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት መንግስታቸውን በተኑ
የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አላሳኒ ኦታራ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር በማንሳት መንግስትን መበተናቸው ተነግሯል።
ያልተጠበቀ ነው የተባለው እርምጃ ምክንያቱ አልተነገረም።
የፕሬዝዳንቱ ዋና ጸሀፊ ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚንስትር ፓትሪክ አቼ ለሰሯቸው ስራዎች ምስጋና አቅርበው እንዳሰናበቷቸው አስታውቀዋል።
ዋና ጸሀፊው አክለውም ባለፉት ዓመታት ሀገሪቱን ሲያገለግሉ የነበሩ ሁሉንም የመንግስታቸውን አባላት ማሰናበታቸውን ገልጸዋል።
ሹማምንቱ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እስከሚሾምና መንግስት እስኪመሰረት ድረስ በጊዜያዊነት ኃላፊነት ላይ ይቆያሉ ተብሏል።
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች ስዕል በፓሪስ ለእይታ ቀረበ
ሮይተርስ እንደዘገበው አይቮሪኮስት ያልተጠበቀና ጥብቅ የመንግስት ለውጥ ማድረግ እንግዳ አይደለም።
ፕሬዝዳንቱ የሚንስትር ሹሞችን በመቀነስ ካቢኔቸውን ለመመጠን ያላቸውን እቅድ ካሳወቁ በኋላ፤ ባለፈው ሚያዚያ ጠቅላይ ሚንስትሩ መልቀቂያ አስገብተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አቼ መልቀቂያቸውን ባስገቡ በሳምንታቸው ግን ዳግም ተሾመዋል።
አይቮሪኮስት በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።
በ2020 የተመረጡት ፕሬዝዳንት አላሳኒ ኦታራ ዳግም በዚህ ምርጫ ይወዳደሩ እንደሆነ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።