ቦብ ማርሌይ የጃማይካ ብሄራዊ ጀግና ተብሎ እንዲሰየም የሀገሪቱ ህግ አውጪ ጠየቀ
ቦብ እርቅና ሰላምን የሚሰብኩ በርካታ የሚዙቃ ስራዎችን በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አድናቂዎች ማድረስ ችሏል
የጃማይካ ፓርላማ ቦብ ማርሌይን “ብሄዋራዊ ጀግና” ተብሎ እንዲሰየም ይጠበቃል
ታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ የጃማይካ ብሄራዊ ጀግና ተብሎ እንዲሰየም የሀገሪቱ ህግ አውጪ መጠየቁ ተሰምቷል።
ቦብ ማርሌይ እንግሊዘኛ ተናጋሪ በሆኑት የካሪቢያን ሀገራት ብሄራዊ ስሜት ከፍ እንዲል በማድረግ ራሳቸውን ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲያወጡ ላደረገው አስተዋጽኦ ነው “ብሄራዊ ጀግና” የሚል ክብር እንዲሰጠው የተጠየቀው።
የጃማይካ ህግ አውጪዎች የሀገሪቱ ፓርላማ ቦብ ማርሌይ ብሄዋራዊ ጀግና ተብሎ እንዲሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እንዲያፀድቅም ተጠይቀዋል።
ህግ አውጪው ቦብ ማርሌይን ብሄራዊ ጀግና ተብሎ እንዲሰየም የጠየቀው ባርባዶስ ሙዚቀኛዋን ሪሃናን ብሄራዊ ጀግና አድርጋ ከሰየመች ከአንድ ወር በኋላ ነው።
የጃማይካ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆነችው ሊዛ ሃና ከሮይተስርስ ጋር በነበራት ቆይታ፤ “ቦብ ማርሌይ በምድር ላይ በነበረው አጭር ቆይታ የዓለም ህዝቦችን አስተሳሰብ እንዲለወጥ በማድረጉ ይህ ክብር ይገባዋል” ብላለች።
"No Woman, No Cry," የሚለው ዘፈኑን ጨምሮ በርካታ የቦብ የሙዚቃ ስራዎች ላይ የተሳተፈችው ማርሻ ገሪፊትስ፤ በሃና ሀሳብ የምትስማማ ሲሆን፤ “ቦብ ማርሌይ ለመላው አለም ብዙ የሰራ ተምሳሌት የሆነ አርቲስት ነው” ብላለች።
“የሙዚቃ አቅም ዓለምን መቀየር ይችላል” የምትለው ማርሻ ገሪፊትስ፤ “ፈጣሪ እንደ ቦብ ማርሌይ ያሉ ሰዎችን የሰጠን ለዚህ ነው” ስትልም ተናግራለች።
የጃማይካ ፓርላማ የቦብ ማርሌይ የብሄራዊ ጀግና ስያሜ ላይ መቼ ውሳኔ እንደሚሰጥ በግልጽ ባይታወቅም፤ ሀገሪቱ በነሃሴ ወርላይ በምታከብረው 60ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ላይ ሊሆን አንደሚችል ተገምቷል።
ታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ በፈረንጆቹ በ1945 በሴንት አን ገጠራማ አካባቢ ከነጭ እንግሊዛዊ አባት እና ከጥቁር ጃማካዊት እናት መወለዱ ይነገራል።
በ12 ዓመቱ ኪንግስተን ወደሚገኘው ተሬንች ከተማ ገባው ቦብ ከበኒይ ዋይለር እና ፒተር ቶሽ ከተባሉ ሙዚቀኞች ጋር በመሆን በመሆን በዓለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት ያገኘውን የሬጌ ሙዚቃ ስራን መፍጠራቸው።
ቦብ ከዛ በኋላም እርቅና ሰላምን የሚሰብኩ በርካታ የሚዙቃ ስራዎችን በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አድናቂዎች ማድረስ አንደቻለም ይነገራል።
የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ ሜላኖባ በተባለ የቆዳ ካንሰር ከታመመ በኋላ በፈረንጆቹ 1981 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።