ከአርሰናል እና ቸልሲ ወደ ሌላ ክለብ ማምራት የሚፈልጉ ብዙ ተጫዋቾች እንዳሉ ሲገለጽ ኒውካስትል፣ ባየር ሙኒክ እና ጁቬንቱስ ዋነኛ ገዢ ክለቦች ይሆናሉ ተብሏል
በጥር የተጫዋች ዝውውር ማን ወደ የት ያመራ ይሆን?
የፈረንጆቹ 2024 ከዛሬ ጀምሮ መግባቱን ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር በይፋ ተጀምሯል፡፡
ይህን ተከትሎም የመጫወት እድል ተነፍጎናል ያሉ ተጫዋች አዳዲስ ክለቦችን በማማተር ላይ እንደሆኑ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
የእንግሊዙ አርሰናል፣ ማንችስተር ሲቲ እና ቸልሲ እግር ኳስ ክለቦች ይጫወቱ የነበሩ ተጫዋቾች በወኪሎቻቸው አማካኝነት ለአንድ ወር በሚቆየው የዝውውር ጊዜ ውስጥ አዲስ ክለብ ለማግኘት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡
የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ እንግሊዛውው ራምሳዴል ወደ ኒውካስትል፣ ስሚዝ ሮው ወደ አስተንቪላ፣ ቶማስ ፓርቴይ ወደ ጁቬንቱስ መዛወር እንደሚፈልጉ ተገልጿል፡፡
የማንችስትር ዩናይትዱ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ወደ ባየርሙኒክ፣ የማንችስተር ሲቲው ካልቪን ፊሊፕስ ወደ ኒውካስትል እና ጁቬንቱስ የመዛወር ፍላጎት አላቸው ተብሏል፡፡
ሌላኛው እንግሊዛው እና ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ጋር ግጭት ውስጥ ያለው ጄዳን ሳንቾ ወደ ቀድሞ ክለቡ ዶርትሙንድ በጥር የተጫዋች ዝውውር ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ዘመኑ ያስቆጠራቸው 850 ግቦች
ከሳንቾ በተጨማሪም ቫን ዴቢክ ወደ ሌላኛው የጀርመኑ ፍራንክፈርት የመዛወር እድሉ ሰፊ ነው የተባለ ሲሆን የቸልሲው ጋላገር ወደ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶትንሀምን የመቀላቀል እድሉ ሰፊ ነውም ተብሏል፡፡
በአጥቂ እየተጨገረ ያለው አርሰናል የብሬንትፎርዱን ኢቫን ቶኒን ሊያስፈርም ይችላል የተባለ ሲሆን ተጨዋቹ ላለፉት ስምንት ወራት በቁማር ምክንያት እገዳ ተላልፎበት ቆይቷል፡፡
ሌላኛው በጥር የዝውውር መስኮት ተፈላጊ ከሆኑ ተጫዋቾች መካከል የፉልሃሙ ተከላካይ ጃኦ ፓልሂናህ ሲሆን አርሰናል፣ ባየርን ሙኒክ እና ሊቨርፑል የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው፡፡
ሌላኛው የቸልሲ ተጫዋች ትሬቪህ ቻሎባህ በክሪስቲያል ፓላስ፣ ሮማ እና ባየርንሙኒክ እየተፈለጉ ካሉ ተጫዋች መካከል ዋነኛው ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ዝውውሩ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ይገመታል፡፡