ኤልጋዚ በፍልስጤም ምክንያት ከሚጫወትበት እግር ኳስ ክለብ ታገደ
ለሜንዝ ክለብ ይጫወት የነበረው ኤልጋዚ በፍልስጤማዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በማህበራዊ ሚዲያ አውግዞ ነበር
ተጫዋቹ ባደረገው ነገር እንደማይጸጸት እና ይቅርታም እንደማይጠይቅ አስታውቋል
ኤልጋዚ በፍልስጤም ምክንያት ከሚጫወትበት እግር ኳስ ክለብ ታገደ።
የሆላንድ ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ኤልጋዚ እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ባለው ጥቃት ምክንያት ንጹሀን እየተገደሉ ነው በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሮ ነበር።
ለጀርመኑ ሜንዝ እግር ኳስ ክለብ ይጫወት የነበረው ኤል ጋዚ አስተያየቱን ተከትሎ ክለቡ በጊዜያዊነት አግዶ አቆይቶትም ነበር።
ይሁንና ተጫዋቹ ባደረገው ነገር እንደማይጸጸት እና ይቅርታም እንደማይጠይቅ ማሳወቁን ተከትሎ ከክለቡ ጋር የነበረው ስምምነት ተቋርጧል።
ኤልጋዚ ከክለቡ ጋር የነበረው ስምምነት መቋረጡን ተከትሎ እንዳለው " የሆነብኝ በጋዛ ባሉ ህጻናት ላይ እየደረሰባቸው ካለው ግፍ እና በደል አንጻር የሚወዳደር አይደለም" ብሏል።
አሁንም እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ድረስ ከፍልስጤማዊያን ጎን ነኝ የሚለው ኤልሃዚ ድጋፉን እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
በጀርመን ለፍልስጤማዊያን እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች እያደጉ ሲሆን የሀገሪቱ ጠበቆች ኤል ጋዚን እና ሌሎችን በጥላቻ እና ለጸብ በማነሳሳት ወንጀል እንደሚከስ ገልጿል።
የእስራኤል- ሀማስ ወይም ፍልስጤም ጦርነት በ27ኛ ቀኑ ላይ ሲሆን በእስራኤል ጦር የተገደሉ ዜጎች ቁጥርም 10 ሺህ ገደማ ደርሷል።