ቻይና ጣልቃ ገብነት ነው ስትል ስምምነቱን ተቃውማለች
ጃፓን እና አሜሪካ የቻይናን የኃያልነት ግስጋሴ ለመግታት የሚያስችል አዲስ ወታደራዊ ትብብር ሊያደርጉ መሆኑን አስታወቁ፡፡
የዓለም አንደኛ እና ሶስተኛ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶቹ አሜሪካ እና ጃፓና የደቡብ ምስራቅ እስያ ቀጣና እንዳይረበሽ በማሰብ ነው ይህን የምናደርገው ብለዋል፡፡
የቻይናን ጠንካራና ከፍተኛ አቅም መፍጠር ስጋት እንዳይሆን ያስችለናልም ነው ቶኪዮ እና ዋሽንግተን ያሉት፡፡
የሁለቱ ሀገራት የውጭ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የበይነ መረብ ውይይት ካደረጉ በኋላ በታይዋንና ቻይና ያለው ሁኔታ ጃፓን ሁኔታዎችን በአንክሮ እንድትከታተል አስገድዷል ተብሏል፡፡
የቶኪዮ እና ዋሸንግተን ባለስልጣናት ዋነኛ የትብብራቸው መነሻ የቻይናን ሃያልነት ለመግታት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሁለቱ ሀገራት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እንዲሁም የሩቅ ምስራቅ ቀጣና ችግር ከገጠመውና ያለመረጋጋት አዝማሚያ ካሳዬ ምላሽ ለመስጠት ያስችለናል ያሉትን ትብብር ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡
የሩሲያ እና ቻይና ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምሳሌ ነው ተባለ
ሚኒስትሮቹ ዓለም አቀፍ ህግጋትን እያከበረች አይደለም ያሏት ቤጂንግ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወታደራዊ እንዲሁም ቴክኖሎጂያዊ ችግሮች ልትፈጥር እንደምትችል መስጋታቸውን ገልጸዋል እንደ ሮይተርስ ዘገባ፡፡
የጃፓን እና የአሜሪካ ባለስልጣናት በቻይና በሺንጃንግ እና በሆንግ ኮንግ ግዛቶች እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ያሳስቡናል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በአንጻሩ የቻይና መንግስትም ጣልቃ “አትግቡ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም ቶኪዮ እና ዋሸንግተን በታይዋን ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር መስራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
ጃፖን ከአሜሪካ በተጨማሪም ከአውስትራሊያ ጋር የመከላከያ ትብብር መፈጸሟ ተገልጿል፡፡
ቤጂንግ ሶስቱ ሀገራት ያደረጉት ስምምነትን በተመለከተ ጣልቃ ገብነት ነው ስትል ተቃውማለች፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ሶስቱ ሀገራት የሃሰት መረጃን መሰረት በማድረግ በቀጣናው ያሉ ሀገራትን የጋራ ትብብር እና ወዳጅነት ለማሳነስ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡