ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁን ወታደራዊ ግንባታ ይፋ አደረገች
ቶኪዮ በወታደራዊ እቅዷ ቻይናን መምታት የሚችሉ ሚሳይሎችን በመግዛት "ለዘላቂ ግጭት" ዝግጁ ለመሆን ወጥናለች።
ሀገሪቱ በወታደራዊ በጀቷ ከአሜሪካ እና ከቻይና ቀጥላ ሦስተኛዋ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ የምታወጣ ትሆናለች።
ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁን ወታደራዊ ግንባታ ይፋ አደረገች።
ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁን ወታደራዊ ግንባታዋን በ320 ቢሊዮን ዶላር መድባለች።
ቶኪዮ በወታደራዊ እቅዷ ቻይናን መምታት የሚችሉ ሚሳይሎችን በመግዛት "ለዘላቂ ግጭት" ዝግጁ ለመሆን ወጥናለች።
ሀገሪቱ ቀጠናዊ ውጥረት እና የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ስጋት ስለሆነባት ነው አዲሱን ውጥኗን ይፋ ያደረገችው።
የማይታሰብ ነው የተባለው የአምስት ዓመት እቅድ ሀገሪቱን ከአሜሪካ እና ከቻይና ቀጥላ ሦስተኛዋ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ የምታወጣ ያደርጋታል።
ጠቅላይ ሚንስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጃፓን እና ህዝቦቿ "በታሪክ ለውጥ ላይ ናቸው" ሲሉ የገለጹት ዝግጅቱ "ለሚያጋጥሙን የተለያዩ የጸጥታ ችግሮች መልሴ ነው" ብለዋል።
በተጨማሪም መለዋወጫ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች በማከማቸት የትራንስፖርት አቅምን እንደሚያሰፋ እና የሳይበር ጦርነት አቅምን እንደሚያዳብር የጃፓን መንግስት አስታውቋል።
የጠቅላይ ሚንስትር ኪሺዳ እቅድ ከፈረንጆቹ 1976 ጀምሮ ሲተገበር የነበረውን ከሀገር ውስጥ ምርት የአንድ በመቶ የወጪ ገደብ በማለፍ የመከላከያ ወጪን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከፍ ያደረገ ነው።
የመከላከያ ሚንስቴር በጀት አሁን ባለው የህዝብ ወጭን በአስር እጥፍ የሚጨምር ሲሆን ጃፓንን የዓለም ሦስተኛዋ ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት መዳቢ እንደሚያደርጋት ሮይተርስ ዘግቧል።
ቻይና በአዲሱ የጃፓን የጸጥታ ስልት ወታደራዊ እንቅስቃሴዋ ላይ የሀሰት ውንጀላ ሰንዝራለች በሚል ወቅሳለች።