የነጻ ጉዞ ቲኬት አገልግሎቱን በ64 አውሮፕላን ጣቢያዎቿ ላይ እንደምትሰጥ ገልጻለች
ጃፓን ጎብኚዎችን ለማበረታታት የአውሮፕላን ቲኬት በነጻ አቀረበች፡፡
የሩቅ ምስራቋ ጃፓን ሀገሯን ለሚጎበኙ ጎብኚዎች ነጻ የአጉዞ ቲኬት እንደምትሰጥ ገልጻለች፡፡
የሀገሪቱ ቱሪዝም ቢሮ እንደገለጸው ጃፓንን ለሚጎበኙ ጎብኚዎች የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ነጻ የጉዞ ቲኬት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
የነጻ ጉዞ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በጃፓን አየር መንገድ በኩል ለሚጓዙ መንገደኞች ሲሆን ዋና ዓላማውም የጎብኚዎችን ቁጥር ለመሳብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በተለይም በገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚጓዙ ጎብኚዎች የበለጠ እና የተሸለ የጉዞ ማበረታቻዎች ተሰጥተዋል፡፡
የአሁኑ የነጻ ጉዞ ቲኬት ዋጋ በጎብኚዎች ለሚጨናነቁ ቦታዎች እፎይታ ለመስጠት፣ ገጠራማውን የሀገሪቱ ቦታዎችን ለማስጎብኘት እና ከቱሪዝም የተሻለ ገቢ ለማግኘት ያለመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ ጎብኚዎች ይህንን እድል ለማግኘት መጀመሪያ በጃፓን አየር መንገድ መጓዝ እና የሀገር ውስጥ በረራዎ ቲኬት መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
አየር ምነገዱ 24 ሰዓት እና ከዛ በላይ በጃፓን ለሚቆዩ መንገደኞች ለሀገር ውስጥ በረራ ያወጡትን ገንዘብ ተመላሽ ያደርጋል፡፡
እንዲሁም የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ታይላንድ፣ ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና ሕንድ፣ ፊሊፒንስ እና ሌሎችም ሀገራት ዜግነት ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል፡፡
በቀጣይም ጃፓን ለተጨማሪ ሀገራት ጎብኚዎች ይህን የነጻ ጉዞ ቲኬት እድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡