ሺንዞ አቤ ከሁለት ከቀናት በፊት ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ሳሉ መገደላቸው ይታወሳል
ጃፓን ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሺንዞ አቤ ግድያ በኋላ ባደረገችው የላይኛው ምክር ቤት ምርጫ ገዥውና ተጣማሪው ፓርቲ አሸንፈዋል።
ምርጫው የላይኛው ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ የተካሄደ ሲሆን ገዥው ፓርቲም ከ 125 ወንበሮች 63 ወንበሮችን አሸንፏል።
የሀገሪቱ ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቀድሞም ቢሆን የማሸነፉን ቅድመ ግምት ተሰጥቶት ነበር። ፓርቲው የሽንዙ አቤን ግድያ ተከትሎ የተሻለ ድጋፍን ማግኘቱም ተገልጿል።
የሀገሪቱ ገዥ ፓርቲ ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ 63 ወንበሮችን ያሸነፈ ሲሆን ተጣማሪው ደግሞ 13 ወንበሮችን አሸንፏል።
የቀድሞው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ከሁለት ቀናት በፊት ለፓርቲያቸው በመቀስቀስ ላይ ሳሉ በሰሜን ምዕራባዊ የሃገሪቱ ክፍል ናራ ከተማ ጎዳና ላይ መገደላቸው ይታወሳል።
ከሰሞኑ የተገደሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዙ አቤ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።
አቤኖሚክስ በሚል ምጣኔ ሃብታዊ ፍልስፍናቸው የሚታወቁት ሽንዙ አቤ፤ ጃፓን በተሻለ የዲፕሎማሲ እመርታ ላይ እንድትደርስ ማስቻላቸውም ይነገራል።