የጃፓኑ የጸረ-ኑክሌር ጦር መሳሪያ ድርጅት የኖቤል ሽልማት አሸነፈ
ከሄሮሽማ እና ናጋሳኪ የኑክሌር ቦምብ ጥቃት የተረፉ ሰዎች የመሰረቱት 'ኒሆን ሂዳንክዮ' የተባለው ድርጅት የ2024ቱ የኖቤል የሰላም ሽልማት በዛሬው እለት አሸንፏል
የኖቤል ሽልማት አሸናፊ 11 ሚሊዮን የስዊዲሽ ክራውንስ ወይም 1 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል
የጃፓኑ የጸረ-ኑክሌር ጦር መሳሪያ ድርጅት የኖቤል ሽልማት አሸነፈ።
ከሄሮሽማ እና ናጋሳኪ የኑክሌር ቦምብ ጥቃት የተረፉ ሰዎች የመሰረቱት 'ኒሆን ሂዳንክዮ' የተባለው ድርጅት የ2024ቱ የኖቤል የሰላም ሽልማት በዛሬው እለት አሸንፏል።
ከሁለቱ የቦምብ ጥቃቶች የተረፉ የአይን እማኞች አለም ከኑክሌር የጦር መሳሪያ ነጻ እንድትሆን እደሜያቸውን ሙሉ ጥረት አድርገዋል።እነዚህ ከጥቃቱ የተረፉት ሰዎች 'ሂባኩሻ' በመባል ይታወቃሉ።
የኖርዋይው የኖቤል ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ "ሂባኩሻ አለም ከኑክሌር የጦር መሳሪያ ነጻ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት እና የኑክሌር ጦር መሳሪያ ድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል እንደሌለበት ምስክር ስለሆኑ የኖቤል የሰላም ሽልማት አግኝተዋል"ብሏል።
"ሂባኩሻ መግለጽ የማይቻለውን እንድንገልጽ፣ የማይታሰበውን እንድናስብ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ በኑክሌር የጦር የደረሰውን ከባድ ጥቃት እንድናውቅ ረድቶናል" ሲል ኮሚቴው ገልጿል።
የኖርዌው የሰላም ኮሚቴው ሊቀመንበር ጆርገን ዋትኒ ፍራይድነስ ሰም ሳይጠቅሱ ኑክሌር የታጣቁ ሀገራት እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቀዋል።
"የዛሬው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ከበፊቱ የበለጠ እጅግ አውዳሚ ነው። የሚሊዮኖችን ሊገድሉ እና በአየር ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
"የኑክሌር ጦር ስልጣኔያችንን ሊያወድም ይችላል።"
ፍራይድነስ ኒሆን ሂዲያንካ እና ሌሎች የሂባኩሻ ተወካዮች ላድረጉት ልዩ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። አሜሪካ ሄሮሽማ እና ናጋሳኪ በተባሉ ሁለት ግዛቶች ላይ በ1945 ያደሰችው የኑክሌር ቦምብ ጥቃት ቀጣይ አመት 80ኛ አመት ይሞላዋል።
የኖቤል ሽልማት አሸናፊ 11 ሚሊዮን የስዊዲሽ ክራውንስ ወይም 1 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል።