“መሳቅ የጠፋባቸው” ጃፓናዊያን ወደ ሳቅ ትምህርት ቤት ለመግበት ተገደዋል
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሶስት ዓመታት ማስክ ሲያደርጉ የነበሩ ጃፓናዊያን ሳቅ ጠፍቶባቸዋል
ይህን ተከትሎም የሳቅ ትምህርት ቤቶች ገበያው ደርቶላቸዋል ተብሏል
ሩቅ ምስራቋ ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ሀገር ናት።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚልም ሀገሪቱ ዜጎቿ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ማስክ ማድረግን ግዴታ አድርጋ ቆይታለች።
የዓለም ጤና ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ወረርሽኝ የመሆን እቅሙን አጥቷል ማለቱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም ጃፓን ለዓመታት ማስክን ሲያደርጉ የነበሩ ዜጎቿን ያለ ማስክ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አሳውቃለች።
ለዓመታት ማስክ በማድረግ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ጃፓናዊያን አሁን ላይ ፈገግ ማለት እና መሳቅ እንደጠፋባቸው ተገልጿል።
መሳቅን የረሱ ዜጎችም እንደቀድሟቸው ፈገግ ለማለት ወደ ሳቅ ትምህርት ቤቶች ማቅናታቸውን ጃፓን ታየምስ ዘግቧል።
እንዴት መሳቅ እንዳለባቸው ትምህርት ለመቅሰም ወደ ትምህርት ቤት ጎራ ያሉ ጃፓናዊያን እንዳሉት ፈገግ ለማለት ሲሞክሩ ፊታቸው ላይ ህመም እንደሚሰማቸው፣ ፊታቸው ሊወድቅ የተንጠለጠለ መምሰል እና ሌሎች አይነት ሁኔታዎች እየተፈጠሩባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የሳቅ ትምህርት ቤቶች በሰልጣኞች መጥለቅለቃቸውን ያሳወቁ ሲሆን ገበያውን ተከትሎም ትምህርት ቤቶቹ ስልጠናቸውን በማስፋፋት ላይ እንደሆኑ ተጠቅሷል።
በቶኪዮ የሳቅ መምህር የሆነው ኬኮ ካዋኖ እንዳለው ባለፉት ጥቂት ቀናት በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች ስለ ሳቅ ለመማር መመዝገባቸው ገልጿል።