ራስን ከተቀጣሪነት ለማውጣት የተከፈለ መስዋዕትነት
ጃፓናዊው የራሱን ስራ ለመጀመር በሚል ላለፉት 20 ዓመታት ነፍስ ማቆያ ምግብ እና አልባሳትን ሲጠቀም ነበር ተብሏል
የ32 ሺህ ዶላር ደመወዝተኛ የሆነው ይህ ሰው ላለፉት 21 ዓመታት ባደረገው ቁጠባ 640 ሺህ ዶላር ቆጥቧል
ራስን ከተቀጣሪነት ለማውጣት የተከፈለ መስዋዕትነት
ጃፓናዊው ሰው ስራ በጥሩ ደመወዝ እና ስራውን ደስ ብሎት እንደጀመረ ይናገራል፡፡ ይሁንና ቀስ በቀስ የሚሰራበት ተቋም የስራ ባህሪ እየተቀየረ መምጣቱን ገልጿል፡፡
በተለይም አሰሪ ተቋሙ ምሽትን ጨምሮ በማንኛውም ሰዓት ስራ ማሰራት መፈለጉን ተከትሎ ስራ ለመቀየር ቢሞክርም የስራ ባህላቸው ተመሳሳይ ይሆንበታል፡፡
ከአሰልቺ የስራ ከባቢ ሁኔታ ራሱን ማዳን የሚችለው ተቀጥሮ መስራቱን ሲያቆም ብቻ መሆኑን ይረዳል፡፡
በዓመት በአማካኝ 32 ሺህ ዶላር ደመወዝተኛ የሆነው ይህ ጃፓናዊ በዚህ ገቢው ጥሩ ኑሮ መኖር የሚችል ቢሆንም የግድ የራሱን ስራ ለመስራት ግን መቆጠብ እንዳለበት ይረዳል፡፡
ከ100 አመት በላይ ለመኖር በተመራማሪዎች የተጠቆመ አስገራሚ ምክረሃሳብ
በመሆኑም ላለፉት 21 ዓመታት ባደረገው ቁጠባ 132 ሚሊዮን የን ወይም 640 ሺህ ዶላር መቆጠቡን አስታውቋል፡፡
ግለሰቡ ይህንን ገንዘብ ለመቆጠብ ብዙ ፍላጎቶቹን እንደገደበ የገለጸ ሲሆን በተለይም ነፍሱን በህይወት ማቆየት የሚያስችሉ ርካሽ ምግቦችን፣ ቅናሽ ያለባቸው ጥራታቸው ዝቅተኛ የሆኑ አልባሳትን ሲጠቀም እንደቆየ ተናግሯል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በተለይም በጃፓን የምግብ ዋጋ እያሻቀበ መምጣቱን ተከትሎ በሳምንት ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ርካሽ የተቀቀለ ሩዝ ብቻ እንደሚመገብ አስታውቋል፡፡
በርካቶች የግለሰቡን ታሪክ ከሰሙ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ግማሾቹ ድርጊቱን ሲያደንቁ ቀሪዎቹ ደግሞ ግለሰቡ ገንዘብ ለመቆጠብ ሲል በበሽታ ሊሞት እንደሚችል እና አሁን ላይ ጤነኛ በመሆኑ እድለኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጥቂቶች ደግሞ የግለሰቡ ውሳኔ ድፍረት እና አለማወቅ መሆኑን ከዚህ ይልቅ ትንሽ ገንዘብ እንደቆጠበ ወደ ንግድ ቢገባ አሁን ካለው የተሻለ ሀብት እና ህይወት ይኖረው ነበር ብለዋል፡፡