ሁሉንም ሴቶች እኩል እወዳለሁ የሚለው ይህ የብዙዎች ባል ዋና ስራው ምግብ ማብሰል እና ልጆችን መንከባከብ መሆኑን ተናግሯል
ስራ ሳይኖረው ሶስት ሚስቶች እና ልጆች ያሉት አባወራ
ሩታ ዋታናቢ የተሰኘው ጃፓናዊ የ35 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ሳፖሮ በተሰኘችው የጃፓን ከተማ ነዋሪ ነው፡፡
ይህ ግለሰብ ሶስት ሚስቶች እና ሁለት ፍቅረኞች አሉኝ ማለቱን ተከትሎ ከጃፓን ባለፈ በመላው እስያ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
ከሶስት ሚስቶቹ ጋር በጋራ እየኖረ መሆኑን የሚናገረው ይህ ግለሰብ ከመጀመሪያ ሚስቱ ሁለት ልጆች ከሁለተኛዋ ሚስቱ ደግሞ አንድ ልጅ በድምሩ ሶስት ልጆች ያሉት ሲሆን ተጨማሪ ልጆችን የመውለድ ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል፡፡
ላለፉት 10 ዓመታት ስራ አልሰራሁም የሚለው ይህ የብዙዎች ባል ሁሉንም ሴቶች በእኩል እንደሚያፈቅር ሚስቶቹም ይህን እንደሚያውቁ ገልጿል፡፡
ግለሰቡ ሁለቱ ፍቅረኞቹ አብረውት እንደማይኖሩ ሶስቱ ሚስቶቹ ግን ተስማምተው በአንድ ቤት በየራሳቸው ክፍል እየኖሩ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ከአንድ ባል ሶስት ልጆችን የወለዱት ሁለቱ ሚስቶች ሁኔታውን ለልጆቻቸው እንዴት ሊያስረዷቸው እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሁኔታውን ለህጻናት ማስረዳት ቢከብድም ሁሉም ቤተሰብ ተመሳሳይ ህይወት እና ታሪክ እንደሌለው እንደሚያስረዷቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ስትወሰልት የተያዘች ሚስት በባሏ እርዳታ የምትወደውን ሰው አገባች
በጃፓን ህግ መሰረት አንድ ሰው ከአንድ ሚስት ወይም አንድ ሴት ከአንድ ባል በላይ ማግባት የማይፈቀድ ሲሆን የሚያገቡ ሰዎችም ቁጥር በየጊዜው እየቀነሰ ይገኛል፡፡
እስካሁን የጋብቻ ማስረጃ እንደሌላቸው የሚናገሩት እነዚህ ሚስቶች በቀጣይ በየተራ ጋብቻ ከፈጸሙ በኋላ መልሰው ፍቺ በመፈጸም ለልጆቻቸው ህጋዊ የቤተሰብ ስም ለማግኘት እንደሚሞክሩም ተናግረዋል፡፡
በአዛውንቶች ብዛት የዓለማችን ቀዳሚ የሆነችው ጃፓን ልጆችን የሚወልዱ ሰዎችን ለማነቃቃት የተለያዩ ማበረታቻዎችን ዘርግቷል፡፡