ፈረንሳዊው በርናርድ አርኖልት በሁለት ቢሊዮን ዶላር ተበልጦ ደረጃውን ለጄፍ ቤዞስ አስረክቧል
ጄፍ ቤዞስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ሆነ፡፡
ላለፉት ወራት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋነት ደረጃን ተቆጣጥረው የነበሩት ፈረንሳዊ የፋሺን ኩባንየ ባለቤት በርናርድ አርናውልት በጄፍ ቤዞፍ ተበልጠዋል፡፡
በርናርድ አርናውልት በኩባንያዎቻቸው የቦርድ አመራር ውስጥ ልጆቻቸውን ማስገባታቸውን ተከትሎ የድርጅቶቻቸው የአክስዮን ዋጋ ቀንሷል፡፡
በአርናውልት አዲስ ውሳኔ ምክንያት የ6 ነጥ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያጡ ሲሆን በአጠቃላይ አዲሱ ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ገቢያቸው እየቀነሰ መምጣቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በተቃራኒው የአማዞን ኩባንያ መስራች እና ባለቤት አሜሪካዊው ጄፍ ቤዞስ የፈረንጆቹ 2024 ከገባ ጀምሮ 28 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል ተብሏል፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሴት ባለጸጋ ፍራንሶይዝ መየርስ ማን ናቸው?
የሀብታቸው መጠንም 205 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ፈረንሳዊ አርናልውት ደግሞ 203 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌላኛው አሜሪካዊ እና የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኢለን መስክ በ202 ቢሊዮን ዶላር በሶተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የፌስቡክ እናት የሆነው ሜታ ኩባንያ መስራች እና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ደግሞ በ169 ቢሊዮን ዶላር አራተኛው የዓለማችን ባለጸጋ ናቸው፡፡
ከጎግል መስራቾች መካከል አንዱ የሆኑት ላሪ ፔጅ በ156 ቢሊዮን ዶላር አምስተኛ እንዲሁም የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራቹ እና ባለቤቱ ቢልጌት በ152 ቢሊዮን ዶላር በስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለውል፡፡