የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኋይት ሃውስ የፎክ ኒውስ ዘጋቢ የሆነውን ጋዜጠኛ መስደባቸው አነጋጋሪ ሆኗል
ፕሬዝዳንት ባይደን ከካቢኔያቸው ጋር ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ወደ ጋዜጣዊ መግለጫው ክፍል ቀርበው ንግግር ካደረጉ በኋላ ፔተር ዶሲ የተባለው የፎክስ ኒውስ ዘጋቢ፤ ስለዋጋ ንረት ጥያቄ ማንሳት ይቻላል ብሎ እንደጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡ ፕሬዝዳንቱም ይህንን የጋዜጠኛውን ጥያቄ ከሰሙ በኋላ አጸያፊ ስድብ እንደተሳደቡ ጋዜጠኛው ራሱ ለጣቢያው ገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንቱ፤ ጋዜጠኛውን አጸያፊ ስድብ ከሰደቡት በኋላ በእጅ ስልኩ ላይ መደወላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጆ ባይደን ከጋዜጠኛው ጋር በነበራቸው ንግግር ስድቡ የግል ሁኔታውን እንደማይመለከት ገልጸውለታል ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ፕሬዝዳንት ባይደን ጋዜጠኛውም ይቅርታ የጠየቁት ቢሆንም ፤ጋዜጠኛው ግን “እኔ ማንም ይቅርታ እንዲጠይቀኝ አልፈልግም”ሲል በቀጥታ ስርጭት ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ከዚህ በፊትም የፎክስ ኒውስ የኋይት ሃውስ ዘጋቢ ሄይን ጃክ ሪች በሩሲያ እና ዩክሬን ሁኔታ ላይ“ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጉዳዩ ላይ የመጀመሪያ እርምጃ እስኪወስዱ እየጠበቁ ነው አንደ” በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ “ምን አይነት የሚያስጠላ ጥያቄ ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዜጣዊ መግለጫዎቻቸው ወቅት ሲኤንኤን ጋዜጠኞችን ሲዘልፉ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ፕሬዝዳንት ደግሞ ቁጣቸውንና ስድባቸውን ወደ ፎክስ ኒውስ ዘጋቢዎች ማዞራቸው ተጠቅሷል፡፡
ሲኤንኤን የዴሞክራቶች፤ ፎክስ ኒውስ ደግሞ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡