አዛውንቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አሁንም የአፍ ወለምታቸው ቀጥሏል
ፕሬዝዳንት ባይደን ከአንድ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያው ጥቁር ሴት መሆናቸውን ተናግረዋል
የፊታችን ህዳር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ፕሬዝዳንት ባይደን ልጅ እያሉ በዴላዊር የተመረጡ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነኝ ብለዋል
አዛውንቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አሁንም የአፍ ወለምታቸው ቀጥሏል፡፡
የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፓርቲያቸው ዲሞክራት የፊታችን ሕዳር ላይ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲወዳደሩ ዋነኛ እጩ አድርጓቸዋል።
የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን ባሳለፍነው ሳምንት ከሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ከሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የፊት ለፊት ክርክር አድርገው ነበር።
በዚህ የምርጫ ክርክር ላይ ፕሬዝዳንት ባይደን መናገር ሲያቅታቸው፣ ቃላትን ለማውጣት እና ትኩረታቸውን ለመሰብሰብ ሲቸገሩ ታይተዋል።
ከሰሞኑ ደግሞ በፊላዴልፊያ ባለ አንድ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “እኔ በጥቁር ፕሬዝዳንት ስር ምክትል ሆኜ ያገለገልኩ የመጀመሪያዋ ሴት ነኝ” ብለዋል ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን አክለውም “በዴላዊር ግዛት ውስጥ በልጅነቴ ሙሉ ለሙሉ ደምጽ ያገኘሁ ብቸኛው ፕሬዝዳንት ነኝ” ሲሉም በቃለ መጠይቃቸው ወቅት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በ4 ቢሊዮን ዶላር ምዝበራ በአሜሪካ የምትፈለገው ኢግናቶቫ ማን ነች?
የ81 ዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሪፐብሊካኑ ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር በቀጥታ ያደረጉትን ክርክር ተከትሎ ከአቋማቸው እና ከአእምሯቸው ጤነንት ጋር በተያያዘ ጫናዎች እየበረቱባው መጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአዕምሯቸው ጤና ምክንያት በዶናልድ ትራምፕ መበለጣቸውን ተከትሎ ከምርጫ ራሳቸውን እንዲያገሉ ቢጠየቁም እስከ መጨረሻው እንደሚፋለሙ ተናረግዋል፡፡
ይህን ተከትሎ ሮይተርስ ዶናልድ ትራምፕን ሊገዳደር የሚችሉ እጩዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ሲል ጥናት አካሂዷል።
በጥናቱ የተሳተፉ አሜሪካዊያን መካከል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ የተሻለ ድምጽ አግኝተዋል።
ከሚሼል ኦባማ በመቀጠል የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ በሁለተኝነት ሲጠቀሱ የካሊፎርኒያው ገዢ ጋቪን ኒውሶም ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።