ጆ ባይደን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የዴሞክራቶች ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ድጋፍ ሰጡ
ባይደን “ድንቅ አጋር” ያሏቸው ካማላ ሃሪስ በእርሳቸው ቦታ ለፕሬዝዳንትነት እንዲቀርቡ እንሚፈልጉ አሳውቀዋል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከአሜሪካ ምርጫ ፉክክክር ራሳቸውን አግልለዋል
ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ያገለሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የዴሞክራቶች ዕጩ ሆነው በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲቀርቡ ድጋፍ ሰጡ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን ዛሬ ማምሻውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በለቀቁት መግለጫ ላይ “ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ጥቅም ሲባል” ራሴን ከ2024 ፕሬዝዳንተዊ የምርጫ ፉክክር አውጥቻለው” ብለዋል።
ባይደን ራሳቸውን ማግለላቸው ተክተሎም ምክትላቸው ካማላ ሃሪስ እሳቸውን ተክተው ለፕሬዝዳንት እንዲወዳደሩ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
“ድንቅ አጋር” በማለት ምክትላቸው ካማላ ሃሪስን ያወደሱት ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን፤ ካማላ ሃሪስን በእርሳቸው ቦታ ለፕሬዝዳንትነት እንዲቀርቡ እንሚፈልጉ አስታውቀዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የዴሞክራት ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲቀርቡም ባይደን ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢን ክሊንተን እና ባለቤታቸው የሆኑት ከዚህ ቀደም ሞክራችን ወክለው ከትራምፕ ጋር የተፎካከሩት ሂላሪ ክሊንተንም ለካማራ ሃሪስ ድጋፍ ሰጥተዋል።
ካማላ ሃሪስ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት፣ ጥቁር እና የእስያ ዝርያ ያላቸው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በአውሮፓውያኑ 2020 ታሪክ ሠሩ።
ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በ2021 ፕሬዚዳንት ባይደን የህክምና ምርመራ ሲያደርጉ ለ75 ደቂቃ ያህልም የአሜሪካ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ማን ሊተካቸው ይችላል?
ሮይተርስ ዶናልድ ትራምፕን ሊገዳደር የሚችሉ እጩዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ሲል ጥናት አካሂዷል።
በጥናቱ የተሳተፉ አሜሪካዊያን መካከል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ የተሻለ ድምጽ አግኝተዋል።
ከሚሼል ኦባማ በመቀጠል የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ በሁለተኝነት ሲጠቀሱ የካሊፎርኒያው ገዢ ጋቪን ኒውሶም ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ሚሼል ኦባማ እስካሁን ፕሬዝዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳላት በይፋ ያልገለጸች ሲሆን ፕሬዝዳንት ባይደን ራሳቸውን ከምርጫው ካገለሉ ግን ፓርቲያቸውን ወክለው ሊወዳደሩ ይችላሉ ተብሏል።