ዮርዳኖስ ዛሬ ልኡል አልጋወራሿን ትሞሽራለች
ልኡል አልጋወራሽ አል ሁሴን ቢን አብዱላህ ዳግማዊ ዛሬ ጋብቻቸውን ይፈጽማሉ

በልኡሉ ሰርግ ለመታደም የሀገራት መሪዎች አማን ገብተዋል
ዮርዳኖሳውያን የልኡል አልጋ ወራሻቸውን ሰርግ እየተጠባበቁ ነው።
መዲናዋ አማንም ለደማቁ ዘውዳዊ ሰርግ ስትዘጋጅ ሰንብታለች።
የልኡል አልጋወራሽ አል ሁሴን ቢን አብዱላህ ዳግማዊ የሰርግ ስነስርአት በዛህራን ቤተመንግስት ነው የሚፈጸመው።
ንጉስ አብዱላህ ዳግማዊ እና ባለቤታቸው ንግስት ሪያና አል አብዱላህ ልጃቸውን ከመረቁና መልካም ምኞታቸውን ከገለጹለት በኋላ የሀገሪቱ ጦር ማርሽ ባንድ ሙዚቃዎች ያቀርባል።
ሙሽራዋ ራግዋ ካሌድ አ ሳይፍ እና ቤተሰቦቿም ከጥቂት ቆይታ በኋል ቤተመንግስት ይገቡና የጋብቻ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሏል።
በቤተመንግስት በሚደረገው ደማቅ የልኡሉ ሰርግ ላይ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ከትናንት ጀምሮ ዮርዳኖስ ገብተዋል።
የኢራቁ ፕሬዝዳንት አብዱል ለጢፍ ረሺድ፣ የማሌዥያው ንጉስ ሱልጣን አብዱላህ ሪያት እና ባለቤታቸው አማን ከገቡት መካክል ይገኙበታል።
የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኳታር፣ ኩዌት እና ኦማን ከፍተኛ አመራሮችም በልኡል አልጋወራሹ ሰርግ ለመታደም አማን እንደሚገቡ ይጠበቃል።
ከ1 ሺህ 700 በላይ የዮርዳኖስ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የአረብ ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች የሚታደሙት የሰርግ ስነስርአት በቀጥታ እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
የቤተመንግስቱ የሰርግ ስነስርአት እንደተጠናቀቀም አዲሶቹ ሙሽሮች ወደ ሁሴኒያ ቤተመንግስት ያመራሉ።
በመንገዳቸው ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ ዮርዳኖሳውያን ሙሽሮቹን አጅበዋቸው በመጓዝ የደስታቸው ተካፋይ ይሆናሉ ነው የተባለው።
aXA6IDQ0LjIwMC4xMDEuODQg ejasoft island