የካናዳው ጠ/ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ለምርጫ ቅስቀሳ በቆሙበት በድንጋይ ተመቱ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢራ ፋብሪካ ጎብኝተው ሲመለሱ ነው ከተቃዋሚያቸው በተወረወረ አንስተኛ ድንጋይ የተመቱት
ጀስቲን ተሩዶ በካናዳ አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላልፈው ነበር
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ለምረጡኝ ቅስቀሳ በቆሙበት በድንጋይ መመታታቸው ተነግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ በአንድ የቢራ ፋብሪካ ጉብኝት አድርገው በመመለስ ላይ እያሉ ከተቃዋሚያቸው በተወረወረ አንስተኛ ድንጋይ እንደተመቱ ነው ቢቢሲ የዘገበው።
ጉዳዩን አስመልክተው ለካናዳው ሲቲቪ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተወረወረው ድንጋይ ትክሻቸው አካባቢ እንደመታቸው ተናረዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በያዘ አውቶብስ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎችም በድንጋይ መመታቸውመ ተነግሯል።
ጀስቲን ተሩዶን ጨምሮ በድንጋይ የተመቱት ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰም ነው ዘገባው ያመላከተው።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 2016 አንዲት ሴት በወረወረችው የዱባ ፍሬ ተመትተው እንደነበረ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ መንግስታቸው የመተማመኛ ድምጽ እንዲያገኝ በማሰብ በካናዳ አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላፈው ነበር።
ለምርጫው የሚያደርጉት ቅሰቀሳ ከኮሮና ክትባ እና ከሌሎች ክለከላዎች ጋር በተገናኘ ሲደናቀፍ የቆየ ሲሆን፤ ከሳምንተ በፊት የተናደዱ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን የምርጫ ቅስቀሳ በማወካቸው ለማቋረጥ ተገደዋል።