ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ በድጋሚ ለመመረጥ በቀጣይ ዓመት እንደሚወዳደሩ ተናገሩ
ካጋሜ ሀገሪቱን 800ሺ ሩዋንዳውያን ከተጨፈጨፉበት የ1994ቱ ዘርማጥፋት ወደ ሰላም እና ልማት በማሸጋገራቸው አለምአቀፍ አድናቆት አትርፈዋል
በሀገሪቱ በፈረንዶቹ 2015 በተካሄደው ህገመንግስታዊ ማሻሻያ፣ በ2000 ስልጣን የያዙት ካጋሜ ከሁለት የስልጣን ዘመን በኋላ ስልጣን እንዲለቁ የሚያስገድደው ህግ ተሽሮ ገደብ የለሽ እንዲሆን አድጓል
የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ በሚቀጥለው አመት በሚካሃደው ምርጫ በድጋሚ ለመወዳዳር እና ሩብ ክፍለዘመን ገደማ የሚሆነውን የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ በፈረንዶቹ 2015 በተካሄደው ህገመንግስታዊ ማሻሻያ፣ በ2000 ስልጣን የያዙት ካጋሜ ከሁለት የስልጣን ዘመን በኋላ ስልጣን እንዲለቁ የሚያስገድደው ህግ ተሽሮ ገደብ የለሽ እንዲሆን አድጓል።
ህጉ በ2017 ስልጣን እንዲለቁ የሚደነግግ ሲሆን ማሻሻያው ለተጨማሪ 10 አመት በስልጣን እንዲቆዩ አስችሏቸዋል።
ፕሬዝደንት ካጋሜ ከፖን አፍሪካው ጀውኔ አፍሪቄ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው በሚቀጥለው አመት ምርጫ የመወዳዳር ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት።
"ሩዋንዳውያን በእኔ ላይ በሚያሳዩት መተማመን ደስተኛ ነኝ። እስከምችለው ድረስ ሁሌም አገለግላቸዋለሁ። በእርግጥም እጩ ነኝ" ብለዋል ካጋሜ።
ካጋሜ በነሐሴ 2017 በተካሄደው ምርጫ 98.63 በመቶ ድምጽ ለሰባት አመታት ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ካጋሜ ሀገሪቱን 800ሺ ሩዋንዳውያን ከተጨፈጨፉበት የ1994ቱ ዘርማጥፋት ወደ ሰላም እና ልማት በማሸጋገራቸው አለምአቀፍ አድናቆት አትርፈዋል።
ነገርግን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በመጨቆን እና ሚዲያን በማፈን ካጋሜን ይተቿቸዋል።
ካጋሜ እነዚህን ክሶች አይቀበሉም።
በ2015 አሜሪካ ካጋሜ የስልጣን ዘመናቸውን እንዳያራዝሙ እና ስልጣን እንዲለቁ መጠየቋ ይታወሳል።