የአሜሪካ ወታደራዊ ሚስጢሮችን በ42 ሺህ ዶላር ለቻይና በገንዘብ የሸጠው ወታደር
ወታደሩ ለቻይና አሳልፎ ከሰጣቸው ሚስጢሮ መካከል የሚሳኤል ምርቶች እና ሌሎች ወታደራዊ ስትራቴጂዎች ዋነኞቹ ናቸው
ቻይና በታይዋን ያሉ የአሜሪካዊው ወታደራዊ ሚስጢሮችን በቀላሉ ማግኘቷ ተገልጿል
የአሜሪካ ወታደራዊ ሚስጢሮችን ለቻይና በገንዘብ የሸጠው ወታደር
ሁለቱ የዓለማችን ልዕለ ሀይል ሀገራት የሆኑት ቻይና እና አሜሪካ ከማይግባቡባቸው ጉዳዮች መካከል የቴክኖሎጂ እና ወታደራዊ መረጃዎች ዋነኛው ነው፡፡
ኮርቤይን ሹልዝ የተሰኘ አሜሪካዊ ወታደር ለቻይና አሳልፉ መስጠቱን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ወይም ኤፍቢአይ አስታውቋል፡፡
ቢቢሲ የኤፍቢአይን ምርመራ ሪፖርት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ስሙ ሹልዝ የተሰኘው ወታደር የአሜሪካንን ጠብቅ ወታደራዊ መረጃዎች ለቻይና አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
መቀመጫውን ሆን ግኮንግ ያደረገ አንድ የቻይና የስለላ ተቋም አባል እንደሆነ የሚታመን ሰው የአሜሪካንን ወታደራዊ መረጃዎች በቀላሉ ተቀብሏል ተብሏል፡፡
ለወንጀለኞች አዲስ ፊት የሚሰጡት የፊሊፒንስ ሚስጢራዊ ሆስፒታሎች
ቻይናም ለዚህ ወታደር 42 ሺህ ዶላር ከፍላለች የተባለ ሲሆን ወታደሩ አሳልፎ ከሰጣቸው መረጃዎች መካከል በእስያ ያሉ የአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች፣ ለታይዋን የተሰጡ የሚሳኤል መከላከያ መሳሪያዎች እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን አሳልፎ እንደሰጠ ተገልጿል፡፡
ወታደሩ ለቻይና አሳልፉ ለሰጠው ጥብቅ ወታደራዊ ሚስጥሮች ተጨማሪ ክፍያ እየጠበቀ እያለ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ወንጀል ምርመራ ቢሮም በግለሰቡ ላይ የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ሊደቅኑ የሚችሉ ጥብቅ ሚስጥሮችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ክስ እንደመሰረተበት በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡