የአትሌቱ የግል አሰልጣኝ ሩዋንዳዊው ጌርቪስ ሃኪዚማ በመኪና አደጋው ህይወታቸው አልፏል
የዓለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት የሆነው ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም ህይወቱ አለፈ።
የአትሌት ኬልቪን ኪፕቱም የግል አሰልጣኝ ሩዋንዳዊው ጌርቪስ ሃኪዚማ በመኪና አደጋው ህይወታቸው ማለፉም ተነግሯል።
የአለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት የሆነው የ24 ዓመቱ ኬልቪን ኪፕቱም እና ሩዋንዳዊው አሰልጣኝ ጌርቪስ ሃኪዚማና በኤልዶሬት-ካፕታጋት መንገድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ መሞታቸውን ተሰምቷል።
ኪፕቱም ባላፈው ጥቅምት ወር ቺካጎ ውስጥ በተደረግ የማራቶን ውድድር 2:00:35 በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለም ክብረ ወሰን መስበሩ ይታወሳል።
አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም የሰበረው ክብረ ወሰን ባለፈው ሳምንት በአለም አትሌቲክስ መጽደቁ ይታወቃል።
አትሌት ኪፕቱም በመጪው ሚያዚያ ወር በሮተርዳም በሚካሄድ የማራቶን ውድድር ከ2 ሰዓት በታች ለመግባት አቅዶ በዝግጅት ላይ እንደነበረም ተነግሯል።
የአትሌቱን ህፈት ተከትሎም የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመልእክታውም፤ ኬልቪን ኪፕቱም ኮከብ ነበር፤ የማራቶንን ክብረወሰን ለመስበር መሰናክሎችን ከጣሱ የዓለማችን ምርጥ ስፖርተኞች አንዱ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።
“አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም ገና 24 አመቱ ነበር ነበር” ያት ፕሬዝዳንቱ፤ በቫሌንሲያ ፣ ቺካጎ ፣ ለንደን እና በሌሎች ትልልቅ ውድድሮች ያሸነፈ ጀግና ነው፤ የአእምሮ ጥንካሬው እና ስነ ምግባሩ ወደር አልነበረውም፤ ኪፕቱም የወደፊት ተስፋችን ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።