ኬንያዊቷ እንስት ያላግባብ ጊዜዬን ወስዷል ያለችውን ትራፊክ ማገቷ ተገለጸ
በናይሮቢ አንድ ትራፊክ ተቆጣጠሪ ወደ እንስቷ ተሽከርካሪ እንደገባ ዘግታበታለች ተብሏል
ይህች ኬንያዊት ትራፊኩ ያደረገውን ድርጊት ለቲክቶክ ተከታዮቿ በተንቀሳቃሽ ምስል ካጋራች በኋላ መነጋገሪያ ሆናለች
ኬንያዊቷ እንስት ያላግባብ ጊዜዬን ወስዷል ያለችውን ትራፊክ ማገቷ ተገለጸ፡፡
ግሎሪያ ንታዞላ የተሰኘችው ኬንያዊት በናይሮቢ እያሽከረከረች እያለ ነበር የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ወደ እሷ የመጣው፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ይህች እንስትም የከተማዋን ትራፊክ ህግ ጥሰሻል በሚል ትራፊኩ እንደቀረባት ተናግራለች፡፡
ትራፊኩም አሽከርካሪዋ ምን ጥፋት እንዳጠፋች እየጠየቀችው በቂ ማብራሪያ ሳይሰጣት እና ያለፈቃዷ ወደ ተሽከርካሪዋ እንደገባባትም ተገልጿል፡፡
ይህ ትራፊክ ተሽከርካሪው መቆም በሌለበት ስፍራ አስቁሞኛል የምትለው ይህች እንስት ምንም ጥፋት እንዳላጠፋች እርግጠኛ ስትሆን በትራፊኩ ድርጊት ማዘኗን እና መቀጣት አለበት በሚል በሩን እንደዘጋችበት ገልጻለች፡፡
ኬንያ አንድ ሺህ ፖሊሶችን ወደ ሀይቲ ለመላክ ተስማማች
ትራፊኩ ጊዜዬን ያላግባብ አቃጥሎብኛል ያለችው ይህች እንስትም ትራፊኩ ከተሽከርካሪዋ እንዳይወርድ በሩን በመቆለፍ ቀኑን ሙሉ አብሯት እንዲውል ማድረጓ ተገልጿል፡፡
እንስቷ የተፈጠረውን ክስተት ተንቀሳቃሽ ምስል ለቲክቶክ ተከታዮቿ ማጋራቷን የገለጸች ሲሆን በመጨረሻም ቲክቶክ የእንስቷን አካውንት አግዶታል ተብሏል፡፡
ክስተቱን ተከትሎ ጉዳዩ በኬንያ ዋነኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን አንዳንዶቹ የእንስቷን ድርጊት ሲያደንቁ ገሚሶቹ ደግሞ ድርጊቱን ተችተዋል፡፡
የኛይሮቢ ግዛት አስተዳድር በበኩሉ የትራፊክ ፖሊሱንም የእንስቷንም ድርጊት ኮንኖ መግለጫ አውጥቷል፡፡