ቀነኒሳ እና ኪፕቾጌ ታዋቂ አትሌቶች ብቻ በሚሳተፉበት የሎንደን ማራቶን ይፎካከራሉ
በዘንድሮው ዉድድር ከመደበኛ አትሌቶች ዉጭ ያሉ ተሳታፊዎች አይታደሙም
በኮሮና ምክንያት ውድድሩን ለመመልከት ወደ ሎንደን ጎዳናዎች የሚወጣ አይኖርም ተብሏል
ቀነኒሳ እና ኪፕቾጌ ታዋቂ አትሌቶች ብቻ በሚሳተፉበት የሎንደን ማራቶን ይፎካከራሉ
የዘንድሮው የሎንደን ማራቶን ‘ኤሊት’ ተብለው በሚጠቀሱ ታላላቅ አትሌቶች ብቻ እንደሚካሄድ የውድድሩ አዘጋጆች አስታወቁ፡፡
ውድድሩን ለመመልከት ወደ ሎንደን ጎዳናዎች የሚወጣ አይኖርም ያሉት አዘጋጆቹ ቀነኒሳ በቀለንና ኬንያዊውን ኤሉድ ኪፕቾጌን መሰል አንጋፋ አትሌቶች ብቻ እንደሚፎካከሩበትና ሌሎች ተሳታፊዎች በ‘ቨርቹዋል’ የሩጫ ዘዴ ብቻ እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
ውድድሩ በመጪው ወርሃ መስከረም መጨረሻ (እ.ኤ.አ ጥቅምት 4) ማዕከላዊ ሎንደን ዌስት ሚኒስትር በሚገኘው ሴንት ጄምስ ፓርክ በዝግ በሁለቱም ጾታዎች እንዲሁም በዊልቸር አትሌቶች ዘርፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ቀነኒሳ በዓለምና በኦሎምፒክ ደረጃ የ5 ሺ እና የ10ሺ ሜትር ርቀቶች የሪከርድ ባለቤት ነው፡፡
ባለፈው ዓመት የበርሊን ማራቶንን በድጋሚ ሲያሸንፍ በኪፕቾጌ ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ በሽርፍራፊ 2 ሰከንዶች ምክንያት ሳይሰብር ቀርቷል፡፡
በመሆኑም በዘንድሮው ሎንደን ማራቶን ብርቱ ፉክክርን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ኪፕቾጌ የውድድሩ የሪከርድ ባለቤት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡