ኡሁሩ ኬንያታ ለዲፕሎማቶች መግለጫ ሲሰጡ የሶማሊላንድ ሰንደቅ ዓላማ መታየቱ ውጥረት ተፈጠረ
በኬንያ የሶማሊያ አምባሳደር የኬንያ ፐሬዝዳንት የመሩትን ስብሰባ ጥለው መውጣታቸው ተንገሯል
የሶማሊላንድ ሰንደቅ አላማ በመታየቱ ለተፈጠረው ቅሬታ ሶማሊያን ይቅርታ እንደምትጠይቅ ኬንያ ገልጻለች
የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ናይሮቢ ለሚገኙ የዉጪ ዲፕሎማቶች መግለጫ በሚሰጡበት ስብሰባ ላይ የሶማሊላንድ ባንዲራ መታየቱ ሶማሊያን አስቆጣ።
በኬንያ የሶማሊያ ኤምባሲ ቅሬታውን የገለጸ ሲሆን ኬንያም ይቅርታ ጠይቃለች።
የኡሁሩ ኬንያታን መግለጫ ለመከታተል ተገኝተዉ የነበሩት በኬንያ የሶማሊያ አምባሳደር መሐመድ አሕመድ ኑር፣ የሶማሊላንድ ተወካይ በስፍራዉ መገኘታቸዉን ሲያዩ ስብሰባዉን ጥለው መውጣታቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል።
የኬንያ ዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይቅርታ ቢልም የሶማሊላንድ አምባሳደር በስብሰባዉ ላይ መገኘታቸውን በተመለከተ ያለው ነገር የለም።
በስብሰባዉ ላይ የሶማሊላንድ ሰንደቅ አላማ በመታየቱ ለተፈጠረዉ ቅሬታ ይቅርታ እንደምትጠይቅ ኬንያ ገልጻለች።
ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ በተመረጡት በሶማሊያዉ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ ማሕሙድ በዓለ ሲመት ላይ ሞቃዲሾ ተገኝተው ነበር።
በግዛት ይገባኛልና በሶማሊላንድ ዕዉቅና ሰበብ የሚወዛገቡት ሶማሊያና ኬንያ እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2020 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን አቋርጠዉ ነበር።
ሶማሊያ ከኬንያ ጫት መግዛትዋን አቋርጣም የነበረ ቢሆንም ሰሞኑን ደግሞ የጫቱን ንግድ ለመቀጠል ተስማምተዋል።