ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት፤ “ለሶማሊያ ይገባል” ሲል ከኬንያ ጋር በምትወዛገብበት የባህር ላይ ድንበር ጉዳይ ላይ ብይን ሰጠ
ኬንያ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛነት ይጎድለዋል በሚል ውሳኔውን እንደማትቀበል ማስታወቋ የሚታወስ ነው
ፍርድ ቤቱ በሶማሊያ የቀረበውን የካሳ ጥያቄ ውድቅ አድርጓል
ኬንያ እና ሶማሊያ የሚወዛገቡበትን የባህር ላይ ድንበር ጉዳይ የተመለከተው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ብይን ሰጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ብይን የሰጠው ሃገራቱ የሚወዛገቡበት የባህር ላይ ድንበር ከኬንያ ይልቅ ለሶማሊያ ይገባል ሲል ነው፡፡
ሶማሊያ ከኬንያ ጋር ዳግም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረግ ጀመረች
ሆኖም ኬንያ ዓለም አቀፍ ህግጋትን በመጣስ የነዳጅና የሌሎች የባህር ውስጥ ማዕድናትን አሰሳ በሉዓላዊ የባህር ይዞታዬ ላይ አድርጋለች ለዚህም ካሳ ይገባኛል በሚል በሶማሊያ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጓል እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፡፡
ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን የማስፈጸም አቅም የለውም፡፡ ሆኖም ማሰሪያ ሆኖ በህጋዊ ውሳኔነት ያገለግላል፡፡
ሃገራቱ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በሚገኘውና በማዕድናት በበለጸገው የባህር ላይ ድንበር የሚወዛገቡት በትይዩ ያለው የሃይቁ አካል ይገባናል በሚል ነው፡፡
የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ናይሮቢ ተገናኙ
ሶማሊያ እ.ኤ.አ በ2014 ነበር የይገባኛል ክሱን የመሰረተችው፡፡
ለሶማሊያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትን ያስተላለፉት የሃገሪቱ ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዑስማን ዱቤ ባህራችንን ለመያዝ ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል ብለዋል፤ ጥረቱ በቀላሉ እንዳልተሳካ በማስታወቅ፡፡
ፍርድ ቤቱን ገለልተኛነት ይጎድለዋል በሚል ደጋግማ የምትከሰው ኬንያ ቀደም ሲልም ውሳኔውን እንደማትቀበል አስታውቃለች፡፡
ሃገራቱ ይገባኛ እያሉ የሚወዛገቡበት የባህር ላይ ድንበር ከ100 ሺ ኪሎ ሜትር ስኩዌር በላይ ይሰፋል፡፡