ፖለቲካ
ኬንያ አራት ቱርካዊ ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች
ኬንያ ይህን ያደረገችው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቱርካውያኑ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ሊታሰሩ ይችሉ ሲል ያቀረበውን ስጋት ወደ ጎን በመተው ነው
መግለጫው ባለፈው አርብ ተላልፈው የተሰጡትን ስደተኞች ስም እና ለምን ተላልፈው እንደተጠሱ በዝርዝር አልገለጸም
ኬንያ አራት ቱርካዊ ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች።
ኬንያ አንካራ ተላልፈው እንዲሰጣት ጥያቄ ያቀረበችባቸውን አራት ቱርካዊ ስደተኞችን አሳልፋ መስጠቷን በትናንትናው እለት አስታውቃለች።
ኬንያ ይህን ያደረገችው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቱርካውያኑ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ሊታሰሩ ይችሉ ሲል ያቀረበውን ስጋት ወደ ጎን በመተው ነው።
ኬንያ አሳልፋ እንድትሰጥ የቀረበላትን ጥያቄ የተቀበለችው በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመኖሩ ነው ያለው የውጭ ጉዳይ እና የዲያስፖራ ጉዳይ መግለጫ አራቱ ቱርካውያን በክብር እንደሚያዙ ማረጋገጫ መቀበሉን ገልጿል።
አምነስቲ ባለፈው ቅዳሜ ስደተኞቹ ተላልፈው የሚሰጡ ከሆነ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሊፈጸምባቸው እንደሚችል እና በኬንያ ውስጥ ያሉ ሁለም ስደተኞች የደህንነት ስጋት መጨመሩን ገልጿል።
ኬንያ እንደገለጸችው ያስጠለላቻውን አብዛኞቹ ከሶማሊያ የሆኑ 780ሺ ስደተኞችን ለመከላከል ቁርጠኝነት አላት።
መግለጫው ባለፈው አርብ ተላልፈው የተሰጡትን ስደተኞች ስም እና ለምን ተላልፈው እንደተጠሱ በዝርዝር አልገለጸም።