ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድና ፕሬዝዳንት ፑቲን በምን ጉዳዮች ላይ ተወያዩ?
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በሩሲያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው
መሪዎቹ ከሁለትዮሽ ጉዳዮች በተጨማሪ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶች ዙሪያ መክረዋል
የእረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
የእረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በሩሲያ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናት ምሽት ነው ሞስኮ የገቡት።
በዛሬው እለትም ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም በወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በክሬምሊን ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለይም ከፈረንጆቹ 2018 ወዲህ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ላይ መክረዋል።
በተለይም በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በስፔስ ሳይንስ፣ በኢነርጂ እና በሌሎችም ዘርፎች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድና ፐሬዝዳንት ፑቲን በመካለኛው ምስራቅ ያውን ጦርነትን አንስተው መወያየታቸውም ነው የተነገረው።
የእረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በዚሁ ወቅት፤ በመካለኛው መስራቅ ያለው ግጭት ከመስፋፋቱ በፊት መቆም እንዳለበት አንስተዋል።
በተጨማሪም አረብ ኤምሬትስ ሩሲያ እነና ዩክሬንን ለማደራደር እያደረገች ባለው ጥረት ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይም ተመካክረዋል።
ፕሬዝዳነት ፑቲን በዚሁ ላይ ሩሲያ እና ዩክሬን እስረኞችን እንዲለዋወጡ አረብ ኢምሬትስ ለመራችው ውጤታም ድርድር አመስግነዋል።
በዚህ አመት ብቻ 9 የእስረኛ ልውውጦችን በተሳካ ሁኔታ ማሸማገል የቻለችው ዩኤኢ በአጠቃላይ በሁለቱም ወገን 2184 እስረኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ችላለች፡፡
በዩክሬን ሩስያ ጦርነት ገለልተኛ አቋም ይዛ የዘለቀችው ዩኤኢ በእስረኞች ልውውጥ በሁለቱ ሀገራት መካከል የገነባቸውን እምነት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና ግጭቱን ለማስቆም ልትጠቀምበት እንደምትፈልግ ትገልጸላች፡፡