ኬንያ የከብት ጠባቂዎች ዝቅተኛ ወርሃዊ ደመወዝን ወደ 71 ዶላር ከፍ አደረገች
ኬንያ ዝቅተኛ የሰራተኛ ደመወዝ ወለልን በ6 መቶኛ ከፍ እንዲል ወስናለች
የኬንያ መንግስት ያልተማሩ የቀን ሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል 62 ዶላር እንዲሆን ወስኗል
ኬንያ የከብት ጠባቂዎች ዝቅተኛ ወርሃዊ ደመወዝን ወደ 71 ዶላር ከፍ አደረገች፡፡
ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኬንያ የተቀጣሪ ሰራተኞች ደመወዝ ለይ ማሻሻያ አድርጋለች፡፡
የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት የሰራተኞችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የኬንያ ሰራተኛ ማህበራት፣ አሰሪዎች እና መንግስት ባደረጉት ድርድር የሰራተኞች ወርሀዊ እና ዕለታዊ ደመወዝ ላይ ጭማሪ እንዲደረግ ተስማምተዋል፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረትም የኬንያ ሰራተኞች የ6 በመቶኛ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ የተስማሙ ሲሆን በሀገሪቱ ዝቅተኛው ደመወዝ 7ሺህ 997 ሽልንግ አልያም 62 ዶላር እንዲሆን መወሰኑን የኬናያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ለአብነትም በኬንያ ለአንድ ከብት ጠባቂ ወይም እረኛ በወር መነሻ ደመወዝ 71 ነትብ 6 ዶላር እንደሚከፈል በህግ ተደንግጓል፡፡
ጀርመን 250 ሺህ ስራ ፈላጊ ኬንያውያንን ለመቀበል ስምምነት ፈጸመች
እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚቀጠሩ የቤት ሰራተኞች ደግሞ 70 ነጥብ 8 ዶላር ዝቅተኛ ወርሃዊ ደመወዛቸው ሆኖ እንዲከፈል ግዴታ ሆኗል ተብሏል፡፡
ሌሊት ላይ የጥበቃ ስራ ለሚሰሩ ተቀጣሪ ሰራተኞች ደግሞ 139 ዶላር ዝቅተኛው ደመወዝ ሆኖ መጽደቁ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ኬንያ ላልሰለጠኑ ሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንደ ሚቀጠሩበት የስራ መስክ ከ62 ዶላር እስከ 150 ዶላር ድረስ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጭማሪውን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የሰራተኞችን ህይወት ለማሻሻል የሰራተኞች ማህበራት አሰሪዎች እና መንግስት ረጅም ጊዜ የፈጀ ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸው ተናግረዋል፡፡