ኬንያ በአንድ ከተማ አንድ የምሽት መዝናኛ ቤት ብቻ እንዲኖር ለማድረግ ማቀዷን አስታወቀች
በኬንያ የአልኮል ተጠቃሚዎች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ መሸታ ቤቶችን እዘጋለሁም ብላለች
አስተዳዳሪዎች በቤት ውስጥ የሚሰሩ የአልኮል መጠጦች ምርትን እንዲቆጣጠሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል
ኬንያ በአንድ ከተማ አንድ የምሽት መዝናኛ ቤት ብቻ እንዲኖር ለማድረግ ማቀዷን አስታወቀች።
ጎረቤት ሀገር ኬንያ የአልኮል ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው በሚል አዲስ አሰራር መዘርጋቷን ገልጻለች።
የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ከግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር በአልኮል ቁጥጥር ዙሪያ ውይይት ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።
- ከአልኮል መጠጦች የማገኘው ገቢ ቀንሶብኛል ያለችው ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ማበረታታት ጀመረች
- በኡጋንዳ 12 ሰዎች ደህንነቱ ያልተረጋገጠ አልኮል ጠጥተው ህይወታቸው አለፈ
እንደ ዘገባው ከሆነ ኬንያ የአልኮል ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለመወሰን በአንድ ከተማ አንድ የምሽት መዝናኛ ቤት ብቻ እንዲኖር ለማደረግ ማቀዷ ተገልጿል።
በየግዛቱ ያሉ የምሽት መዝናኛ ቤቶችን ቁጥር በመቀነስ የአልኮል ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለመቀነስ ማሰቧ ተጠቅሷል።
ይሁንና በኬንያ ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያለው በቤት ውስጥ የሚመረቱ የአልኮል ምርቶች መኖራቸው እንደሚያሳስባቸው ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሪጋቲ ጋቻጉዋ ተናግረዋል።
የግዛት አስተዳዳሪዎች የመሸታ ቤቶች ንግድ ፈቃድ እንዳያድሱ ያሳሰቡት ጋቻጉዋ ቀስ በቀስ የአልኮል መሸጫ ቤቶችን ቁጥር የመቀነስ እቅድ መያዙንም አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በኬንያ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ የምሽት ቤቶች የስራ ሰዓት ላይ ማዕቀብ የመጣል እቅድ መያዙም ተገልጿል።
ኬንያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ በአንጻራዊነት የአልኮል ዋጋ ከፍተኛ የሆነ ሲሆን አንድ ላገር ቢራ እስከ ሶስት ዶላር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛል።