የኬንያ ፍርድ ቤት ለ145 አማኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት ናቸው ያላቸውን ፓስተር ዋስትና አገደ
በኬንያ በረሀብ የሞቱ አማኞች ቁጥር ከ133 ወደ 145 ከፍ ብሏል
ተጠርጣሪዎች ምርመራውን አደጋ ላይ ይጥላሉ በሚል ስጋት ዋስትና እንደማይፈቀድላቸው ተነግሯል
የኬንያ ፍርድ ቤት ለ145 አማኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት ናቸው ያላቸውን ፓስተር ዋስትና አገደ፡፡
የኬንያ ፍርድ ቤት ተከታዮቻቸው ራሳቸውን እንዲያስርቡ ትእዛዝ አስተላልፈዋል ያላቸውን ፓስተር ፖል ማኬንዚ የዋስትና መብት ውድቅ በማድረግ የእስር ጊዜውን ለ30 ቀናት አራዝሟል።
ማክሰኞ እለት የሟቾች ቁጥር ከ133 ወደ 145 ከፍ ብሏል የተባለ ሲሆን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም ተብሏል።
የኬንያ ፖሊስ ራሱን "እየሱስ ነኝ" ብሎ የሚጠራውን ግለሰብ ለማብራሪያ ጠራ
ባለስልጣናት የማኬንዚ ተከታዮች በሚኖሩበት ጫካ ውስጥ ጥልቀት በሌላቸው መቃብሮች ውስጥ አስከሬን እየፈለጉ ነው።
የጉድ ኒውስ ዓለም አቀፍ መሪ የሆኑት ማኬንዚ ራሳቸውን ለፖሊስ አሳልፈው ከሰጡ በኋላ እስካሁን ድረስ አቤቱታ እንዲያቀርቡ አልተፈቀደላቸውም።
የፓስተሩ ጠበቃ ጆርጅ ካሪዩኪ ፓስተሩ ከምርመራው ጋር እየተባበሩ ነው ብለዋል።
የኬንያ ሙሰኞች ከመንግስትና ህዝብ የመዘበሩትን ገንዘብ በሀገር ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠየቁ
በሞምባሳ በተደረገው ችሎት ማኬንዚ እና ከሟቾች ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት ሌሎች 17 ሰዎች ምርመራውን አደጋ ላይ ይጥላሉ በሚል ስጋት ዋስትና እንደማይፈቀድላቸው ተነግሯል።
ጠበቃ ዊክሊፍ ማካሴምቦ በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።
ማካሴምቦ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "ፍርዱ በህግ የተፈቀደ አይደለም። የደንበኞቻችንን ህገ-መንግስታዊ መብት ይጥሳል" ብለዋል።
ማኬንዚ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሁለት ህጻናትን በረሀብ እና በአፈና ተጠርጥረው ተይዘው የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን በዋስ ተለቀዋል።